የኦርቶዶክስ መዝሙር አልበም የማገኝበት channel ወይም bot ካለ እባካችሁ ጀባ በሉኝ
Apr 17, 2024✞ ደም ግባት አልባ ✞ ጌታዬ ሆነ ደም ግባት አልባ ጀርባው በጅራፍ ስለኔ ደማ የኔን መገርፍ እርሱ ተገርፎ ክብር አለበሰኝ እርሱ ተገፎ (፪) በሐሰት ሸንጎ ወጥመድ ተጠምዶ ጌታ ተያዘ ህይወቴን ፈቅዶ ክፉዎች ቢያዩት እንደ ወንበዴ ለኔ ግን ሆኗል መዉጫ መንገዴ(፪) ታስረኃል ስለኔ ኢየሱስ መድኅኔ(፪) አገቱኒ ከለባተ ብዙኀን ወአኀዙኒ ማህበሮሙ ለእኩያን አገቱኒ ከለባተ ብዙኀን አዝ= = = = = ሲዘብቱበት ምራቅ ሲተፉ የማይደፈር ደፍረው ሲዘልፉ በከበቡት ፊት ቃል ከለከለ እኔ እንድናገር እርሱ ዝም አለ(፪) ታርደኃል ስለኔ ኢየሱስ መድኅኔ(፪) ቀነዉኒ እደውየ ወእገርየ አዝ= = = = = ሕይወት መንጭቷል ተወግቶ ጎኑ ለከሳሾቹ ተርፏል ማዳኑ እጅ እግሩን ምስማር ሲቸነክረዉ የሞትን እሾህ ከኔ ነቀለው(፪) ተወጋ ስለኔ ኢየሱስ መድኅኔ(፪) ወወደዩ ሃሞተ ውስተ መብልየ ወአስተዩኒ ብሂአ ለፅምእየ ወወደዩ ሃሞተ ውስተ መብልየ አዝ= = = = = እርቃኑን ሆኖ ፈተለው ልብሴን አንዲሁ ወዶኝ ጠጣ ሆምጣጤን በምህረቱ ጠል ነብሴን አርክቶ አለመለመኝ አርሱ ተጠምቶ(፪) ተጠማ ስለኔ ኢየሱስ መድኅኔ(፪) ሊቀመዘምራን ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮ @yamazemur_getemoche ╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯