Hi guys Selam i'm boy and betam aynafar negn ena aynafarneten lematfat mn ladrg?
Apr 14, 2024አይን አውጣ መሆን ነዋ! ይህን ስልህ.. አይናፋር የሆንከው ሳትፈልግ ነው። ታዲያ በፍላጎትህ ደፋር ለመሆን ምን የሚከለክልህ ነገር አለ? እኔ ባንተ መንገድ ካለፉ ሰዎች አንዱ ነበርኩ። አልሐምዱሊላህ ዛሬ በብዙ መድረኮች ወጥቶ የመናገር እድሉ ያለኝ ሰው ነኝ። ይህን ድፍረት ያገኘሁበት የመጀመሪያው ጊዜ የዘጠንኛ ክፍል ተማሪ ሳለሁ የመጀመሪያው የትምህርት ቀን ላይ ፍርሃቴን ለመስበር እየተሳቀቅኩ እጄን አውጥቼ የተናገርኩበት እለት ነበር። በዚያች ቅጽበት ከቀኝና ግራ ብብቴ መሃል ያላበኝን ላብ መናገር አልችልም። ከብብቶቼ አባይ ወንዝና አማዞን ወንዝ ነበር የወረዱት¡ ከራሴ ጋር ንትርክ ውስጥ ገብቼ እጄን አውጥቼ የመለስኩበት እለት ነበር። ይኀው ከዚያ በኋላ ግን 12 እስክጨርስ በራስ መተማመኔን እና በክፍል ውስጥ ያለኝን ተሳትፎ አይተው መርጠውኝ የክፍል አለቃ በመሆን አሳለፍኩ። ከ10ኛ-12ኛ ክፍል ተማሪ ሳለሁ ህጋዊ የተማሪዎች ምርጫ ተደርጎ በከፍተኛ ድምጽ በማሸነፍ ለ3 አመት የሃይስኩላችን ጠቅላይ ተወካይ በመሆን አሳለፍኩ። ጊቢም በተመሳሳዩ የክፍሌ ተወካይ በመሆን አሳለፍኩ። ይህ ሁሉ በራስ መተማመን የመጣው ከዛች የዘጠንኛ ክፍል እጅ አውጥቶ የመመለስ ትግል በኋላ ነው። ከቻልክ በራስ መተማመንህን የሚጨምሩልህን ነገሮች አድርግ። (ማወቅ ያለብህ በራስህ ለመተማመን የምዘረዝርልህ ነገሮች መኖራቸው ግዴታ አይደሉም። ነገር ግን እንደ ግብአት እንድትጠቀማቸው ነው) - ከፈጣሪህ ተቃረብ - ለራስህ ይጎድለኛል ብለህ የምታስባቸውን ነገሮች ማሟላት ከቻልክ አሟላ፤ ካልቻልክ እስኪሟሉልህ #ባለህ_ተብቃቃ - ከጥሩ ሰዎች ጋር ተዋወቅ/ዋል - አሪፍ ልበስ/ጫማ ወይም ያለህን ልብስ/ጫማ ንጹህ አድርገህ ልበስ - የሰውነትና ጸጉርህን ንጽህና ጠብቅ - ከሴት ጋር ብዙ አታውራ - ከሁሉ ጋር አትታይ - ሁሉ ቦታ አትታይ - ሰፖርት ላይ ዘውትር - ከሰው ጋር ተከባብረህ ኑር - በጣም ለመረጋጋት ሞክር (በንግግርም በተግባርም) - ሽቶ ሳታበዛ ተጠቀም በተረፈ... ከማን ነው የምታፍረው? እንዳንተው ከሚበላ፣ ከሚጠጣና ከሚጸዳዳ ሰው ለምን ታፍራለህ? አንተ የያዝከውን ማሰቢያ ጭንቅላት ከያዘ ሰው ምን ያስፈራሃል? እውነት ልንገርህ እኔ የትኛውም መድረክ ላይ ስወጣ ከፊቴ ያሉትን ተመልካቾች ህይወት እንደሌላቸው ግዑዛን እያሰብኩ ነው የማወራቸው። ስለዚህ አትፍራ። ዛሬ የምትወስደው አንድ ትንሽ እርምጃ ነገህን የምታሳምርበት መሆኑን እወቅ። በል ወደ መጀመሪያው እርምጃ! መልካም ጊዜ! Btw I am not a motivational speaker😁 But at least this may help you.. I think.. 🤷🏽♂
Apr 16, 2024