ሰላም ለሁላችሁም እንዴት ናችሁልኝ ጥያቄ ነበረኝ እና እስኪ እንወያይበት ሀሳባቹን አሳውቁኝ🙏🙏 ሐዋርያት 3 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁶ ጴጥሮስ ግን፦ ብርና ወርቅ የለኝም፤ ይህን ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ፤ በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሣና ተመላለስ አለው። ⁷ በቀኝ እጁም ይዞ አስነሣው፤ በዚያን ጊዜም እግሩና ቍርጭምጭምቱ ጸና፥ ⁸ ወደ ላይ ዘሎም ቆመ፥ ይመላለስም ጀመር፤ እየተመላለሰም እየዘለለም እግዚአብሔርንም እያመሰገነ ከእነርሱ ጋር ወደ መቅደስ ገባ። እስኪ ይሄንን ነገር አስረዱኝ በዚያን ጊዜ ሀዋሪያት በቃል ብቻ ተናግረው ሰውን ይፈውሱ ነበር አሁንስ እኛ መፈወስ አንችልም በቃል ብቻ ? እንዲሁም ደግሞ አሁን ለይ ፀበል እምነት እየተባለ ነው በኦርቶዶክስ ዕምነት የሚዳነው ነገር ግን በሀዋሪያት ዘመን አልነበረም ይሄ መንገድ ታድያ አሁን ከየት አምጥተነው ነው?🤔
Apr 14, 2024ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐ 9 ዐይነ ስውሩን ሰው ጭቃ በዐይኖቹ አድርጎ በሰሊሖምም መታጠቢያ ታጠብ ብሎት የፈወሰው ታዲያ ከየት አምጥቶት ነው 😭
Apr 14, 2024