ክርስቶስ ምስክሬ አፈቀርኩኝ እኮ። 22 ዓመቴ ነዉ በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ አፈቀርኩኝ። እና አሁን ጥያቄዬ አንዴት ልንገራት ነዉ? እሷም እንደምታፈቅረኝ እርግጠኛ ነኝ ነገሩ ካንተ ይምጣ ነዉ። እንዲህ ስንገባበዝ በኋላ ላይ እንዳይፀፅተኝ ልነግራት ወስኛለሁ። በአካል ነበር ያሰብኩት ግን አሁን ላይ ተራርቀን ነን ያለነዉ። በፅሁፍ ልንገራት? ቮይስ ላስቀምጥላት? ልደዉል ብል ማዉራት አልችልም። የምር አትቀልዱ እባካችሁ ወንድማችሁን እርዱኝ ግራ ቢገባኝ ነዉ። ፍቅር ግን ይመቸው ደስ የሚል ስቃይ ነዉ ሲሉ እሰማ ነበር አሁን ግን አረጋገጥኩት። አመሰግናለሁ❤
Apr 11, 2024እሺ " የክርስቶስ " ስም ታዲያ ምን ያድርግ ? እንግዲኽ የክርስቶሰወ ከኾንክ ራሱ ክርስቶስ በአንዳች አትማሉ ብሎናል በሰማይም ቢሉ በምድር ደግሞም በጸጉርኽ ! ! ተው እባክኽ ስሙን አትቀልድበት !!
Apr 13, 2024