ሰላም ሰዎች እኔ 21 አመቴ ነው እና ፍቅረኛየ ጋ በዙ አመት ቆይተናል እና አሁን ላይ እርግዛለች እኔ እንድንወልደው ነው ምፈልገው እሳ ግን አትፈልግም እና በተሰቦቾ ቢያዉቁ እንደሚገሏት ነው ምትነግረኝ እሷ ተማሪ ናት እኔ ስራ አለኝ ግን እንደማይበቃ ገቢው ታምናለች ምን ትመክሩናላቹ
Apr 11, 2024ራስህን አሳምነህ ግባ ወንድሜ.... ኩሊ ሰርቼም ቢሆን ልጄን አሳድጋለው ብለህ እመን እግዚዓብሄር የፈቀደለት ነው የሚሆነው እና አንዴ ጠይቀህ ስጦታውን ሰጥቶሃል ስለዚህ መግፋት(ማስወረድ) ሳይሆን በደስታ ተቀብለህ ተግዳሮቶችን መጋፈጥ ነው.... እድለኛ ነህ እውነቱን ነው የነገረችህ ስራህ አይበቃም ምናምን ያለችው ማለቴ ነው ልጅ ሲኖርህ ገንዘብን አታልፍም አባቴ ለልጄ ለሚስቴ ብለህ ማግኘት ያለብህ ነገር ላይ መሰገጥ አለብህ.... I have a friend his gf pregnant when he was 20 እና ሳምንት ስጪኝ አላት ገዳም ሄዶ እየተፀበለ የጥሞና ጊዜውን ወሰደ ፈጣሪውን አመሰገነ ተመልሶ መጣ የውሀ ዝርጋታ ነበር ስራው አብረን እናሳድገው አላት ያገኘውን ስራ ነው የሚሰራው ብታይ እጁ ላይ 100 ሺ እያለው እቃ ከመኪና ላይ ሸክም ያወርድ ነበር አሁን እሱ 28 ደርሷል እና ሁለተኛ ደግሞ የግል ነው የሚያስተምራቸው ምናምን በቃ ለነሱ ብሎ ነው የሚኖረው.... እሷን ለማሳመን አንተ መጀመርያ ማመንና ቆርጠህ መነሳት አለብህ look 20 ዓመቱ ላይ ውለጂው ሲላት 5 ሳንቲም አልነበረውም ልጁን ለማሳደግ ግን ደሙን እንደሚሰጥ ቆርጦ ነበር ብሎም እግዚዓብሄር የፃፈለትን ነው የሚኖረው ማለት በአቅምህ ስለዚህ ጤነኛ ሆኖ ማደጉና ታታሪ አባት እንዳለው ማወቁ በራሱ ትልቅ ነገር ነው.... አንዳንዶች ዘመናቸው የሚያልፈው ቤት፣ መኪና፣ ተንደላቆ የሚያድግበትና ለውርስ የሚሆን ገንዘብ እናፍራ እያሉ ነው ያ ስህተት ነው ቢሆን እኮ ደስ ይላል ግን ደግሞ ፈጣሪ ተንደላቀህ አትኑር ካለው ሀብት ላይ ተወልዶም ጤና የሌለው ይሆናል.... so መጀመርያ አንተ እመንበትና እርሷን አሳምናት ቤተሰቦቿ ቢቆጡ ለ1 ወይም 2 ሰዓት ነው ልጇን ብታስወጣው ግን የዘላለም ቁጭትና ጠባሳ በው🙏
Apr 11, 2024