for orthodox christians ለ ልደታ ( ለእመቤታችን ልደት) የሚሆን ግጥም ስነፅሑፍ ካላችሁ ላኩልኝ
Apr 08, 2024"ዮም ፍስሐ ኮነ" ዮም /ፍስሐ ኮነ/(፪) በእንተ ልደታ ለማርያም በባርነት ሳለን - - - ፍስሐ ኮነ ኃጢአት በአለም ነግሳ - - - ፍስሐ ኮነ በድንግል መወለድ - - - ፍስሐ ኮነ ቀረልን አበሳ - - - ፍስሐ ኮነ እግዚአብሔር መረጠሸ - - - ፍስሐ ኮነ ልትሆኚው እናቱ - - - ፍስሐ ኮነ ይኸው ተፈፀመ - - - ፍስሐ ኮነ የዳዊት ትንቢቱ - - - ፍስሐ ኮነ አዝ = = = = የሔዋን ተስፋዋ - - - ፍስሐ ኮነ የአዳም ዘር ህይወት - - - ፍስሐ ኮነ የኢያቄም የሐና - - - ፍስሐ ኮነ ፍሬ በረከት - - - ፍስሐ ኮነ ምክንያተ ድኂን - - - ፍስሐ ኮነ ኪዳነምህረት - - - ፍስሐ ኮነ ድንግል ተወለደች - - - ፍስሐ ኮነ የጌታዬ እናት - - - ፍስሐ ኮነ አዝ = = = = በሔዋን ምክንያት - - - ፍስሐ ኮነ ያጣነውን ሰላም - - - ፍስሐ ኮነ ዛሬ አገኘነው - - - ፍስሐ ኮነ በድንግል ማርያም - - - ፍስሐ ኮነ የምስራች እንበል - - - ፍስሐ ኮነ ሀዘናችን ይጥፋ - - - ፍስሐ ኮነ ተወልዳለችና - - - ፍስሐ ኮነ የአለም ሁሉ ተስፋ - - - ፍስሐ ኮነ
Apr 11, 2024