Eski help me kechalachu be idea Ye 5k birr teketari serategha negh this yr new yejemerkut sraye adkami nee yaw gn yesra lmd slelelegh be werede drmoz eyeseraw new so chhru esu aydelem yemnorew ke family ga new destegha endihonu efelgalew ena lezam yechalkutn adergalew Enesu yemifelgut tmhrten endecheresku agbche endweta nbr eskeza )malt eske graduation dres selam nbr gn enesu endasebut ene beza menged lhed alchalkum actually bf nberegh eske marriage yemasbw but alhonem beka mnm madreg alchalkum ena family ahun lay tru aydelum fit eyenesugh metu yihen melmed betam kebedegh So beka risk wesje kebet lweta new ena gn sasbew bezi demoz plus set hoghe negerochn endet handle endemareg alawkm betam chemkoghal 😟
Mar 31, 2024ተከራይተሽ የሚል ዐሳብ በግሌ የለኝም ! በተለይ ነዋሪነትሽ በአዲስ አበባ ከኾነ !! ደሞዝሽ ከቤት ኪራይ ያለፈ አይደለም ! ተከራይተሽ ብትወጪ በቀጣይ መጋፈጥ የሚገጥምሽን የሕይወት መስተጋብር ለመወጣት ስትይ ምን አልባትም ወዳልተፈለገ የፍቅር ግንኙነት አልያም ያልተገባን ውሳኔ ልትወስኚ ትችያለሽ ! ! መጠንቀቅ አይከፋም !! ትዳር እነሱ በፈለጉት ሰአት የሚገነባ የእቃ እቃ ቤት አይደለም ! ለመኖሪያ የሚኾን ምድራዊን የጭቃ ቤትስ እንኳ ለመገንባት መንግስት የግንባታን ፈቃድ እስኪሰጥ ድረስ ጣጣው ብዙ ነው ። መኝታው ንጹህ የኾነ ክቡሩን ጋብቻማ ለመመስረት ፈቃደ እግዚአብሔርን ከመጠየቅ አንስቶ ለትዳር የምንመርጠውን ሰው በጥቂቱም እንኳ ለማወቅ ጊዜ አስፈላጊ ነው ። ምን አልባትም ቀድሞ ተማሪ ኾነሽ ሳለ ከወንድ ጋር እንድትታዪ የማይፈልጉ ቤተሰቦች ይኾናሉ ከተመረቅሽ በኋላ ወዲያውኑ ትዳር እንድትይዢ የሚፈልጉት ( ከየት ይመጣል 😁 ) በእነሱ በኩል ኾነን ነገሮችን ብንመለከት ዐሳባቸው እውነት ያላቸው ቢኾንም ችኩልነት ግን ይታይባቸዋል ! መቸኮላቸውና ጸባያቸው መቀያየሩ አንቺን ወደ ፈለጉት ሕይወት በግድም አልያም ውድም እንድትገቢ የሚገፋፋ ሲኾን በአንጻሩ ሕይወትሽን ሊያዘበራርቅ የሚችል መኾኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል ! ( በቀደም ራሱን ያጠፋው ኳስ ተጫዋች እንደ ምሳሌ ሊነሳ ይችላል ቤተሰብ በልጆች ሕይወት ውስጥ የመወሰን ድርሻ ቢኖራቸውም በትዳርና በፍቅር ሕይወታቸው ለሚወስኑላቸው ውሳኔ ግን በእጅጉ ሊጠነቀቁና ከፍላጎታቸው እና ከስሜታቸው በላይም ሊኾኑበት እንደሚገባ አመላካች ነው ) በመኾኑም አንቺ ታገሺ ። እየገላመጡሽም እያኮረፉሽም ቢኾን በትኅትና እና በፍቅር ልጅ ኹኝላቸው ! ጸሎት አድርጊ ! ክርስቶስ ያሰረልንን ዲያቢሎስ በገዛ ፈቃዳችን ፈትተን የለቀቅንበት ዘመን እንደመኾኑ ከፈቃደ ሥጋችን ከምንቀበለው ፈተና ባሻገር ዲያቢሎስ በቤተሰቦቻችን ላይ እያደረ እንኳ በእጅጉ የሚፈትነን ጊዜ ነው ! ! ( ማሳሰቢያ ለኦርቶዶክሳዊያን :- መዳን ትፈልጋላችኹ ? ዓይናችኹን ክፉ ከማየት ጆሮአችኹን ክፉ ከመስማት አንደበታችኹን ክፉ ከመናገር ጠብቁ :- ይኽን ስል በዚኽ ቻናል ላይ ለሚጠየቁ ጥያቄዎች ለሚሰጡት የባለጌ ምላሾች ጆሮ አለመስጠትን የሚያካትት ሲኾን በተጨማሪ መላሾቹን ባለጌዎችም ብሎክ በማድረግ ዓይናችኹን በመጠበቅ የራሳችኺ አደሚን ኹኑ ) እንደ ቀልድ ባታዩት ደስ ይለኛል የተናገርኩትን !
Apr 04, 2024