As wr wb Age 23 Selat ly bezum aydelehum gys ena bezi b Ramadan wekt rasu meghrib,esha,terawi enezin becha nw yemisegdw ena malet yefelekugn le selat yemiyanesasagn negr ( audio,video) lakulign pleas 😔 Qur'an alkerewum ena le selat bota endinoregn yemiyareg negr pleas betam nw yemichenkegn
Mar 30, 2024ወአለይኩምአሰላም ወረህመቱሏሂ ወበረካቱህ። ወንድሜ በትዕግስት አንብበው እና ባለህበት ሁኔታ ሞት ቢመጣ ምን እንደሚሰማህ አስተውል እና ወደ መስጂድ የሚመላለስ ጓደኛ ያዝ። አላህ ያግራልህ። በውስጥ ማውራት ከፈለግክ በ0704905961 ቴሌግራም ላይ የሰላት ወቅቶች ግዴታ የሆኑ ሰላቶች በሀያ አራት ሰዐት ውስጥ አምስት ሲሆኑ ሱቢሂ ,ዙሁር ,አስር ,መግሪብ, ዒሻ ይባላሉ ለእያንዳንዱ ሰላት የተወሰኑ ወቅቶች አሏቸው፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፡- ‹‹ሶላት በምእምናን ላይ በጊዜያት የተወሰነች ግዴታ ናትና፡፡›› (አል ኒሳእ:1ዐ3) ወቅቱ ሳይደርስ የሚሰገድ ሰላት ተቀባየይነት የለውም፡፡ ስለ ሰላት ወቅት ከሚጠቅሱ ሀዲሶች ሰላቶችን በወቅቶቻቸው መስገድ አላህ ዘንድ በጣም ከሚወደዱና ብልጫ ካላቸው ስራዎች የሚመደብ ነው፡፡ ነብዩ ( ﷺ) አላህ ዘንድ በጣም የሚወደድን ስራ ሲጠየቁ “ሰላቶችን በወቅቶቻቸው መስገድ” በማለት መልሰዋል:: [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል] የሱብሂ ሰላት ወቅት ነብዩ ( ﷺ)እንዲህ ሲሉ አስተላልፈውልናል :- የሱብሂ ሰላት ወቅት ጐህ ከቀደደ ጀምሮ ፀሐይ ልትወጣ ትንሽ እስከሚቀራት ድረስ ነው፡፡” [ሙስሊም ዘግበውታል] እነዚህ ለሰላት የተደነገጉ ወቅቶች በመሆናቸው ማንኛውም ሙስሊም የሰላት ወቅቶችን እየተጠባበቀ ሳያዘገይ በተወሰነላቸው ወቅቶች ሊሰግድ ይገባል፡፡ አላህ ሰላትን የሚያዘገዩን ሰዎች እንዲህ በማለት ዝቶባቸዋል፡- ‹‹ከእነሱም በኋላ ሶላትን ያጓደሉ (የተዉ) ፍላጎቶችንም የተከተሉ መጥፎ ምትኮች ተተኩ! የገሀነምንም ሸለቆ በእርግጥ ያገኛሉ፡፡›› (መርየም 59) በሌላ አንቀፅም እንዲህ ብሏል፦ ‹‹ወዮላቸው ለሰጋጆች፡፡ ለእነዚያ እነርሱ ከስግደታቸው ዘንጊዎች ለኾኑት፤ (ሰጋጆች) ፡፡›› (አል ማዑን 4-5) የዙህር ወቅት ነብዩ ( ﷺ)እንዲህ ሲሉ አስተላልፈውልናል :- “የዙህር ወቅት ፀሐይ ወደ ምዕራብ ዘንበል ካለችበት ሰዓት ጀምሮ የአንድ ሰው ጥላ ከቁመቱ እኩል ሊሆን ትንሽ እስኪቀረው ድረስ ነው፡፡" [ሙስሊም ዘግበውታል] የዙህር ወቅት ፀሐይ ከእኩለ ሰማይ ወደ ምዕራብ ዘንበል ስትል ጀምሮ የአንድ ነገር ጥላ ከርዝመቱ እኩል እስከሚሆን ድረስ ሲሆን በመጀመሪያው ወቅት ላይ መስገድ ግን የተወደደ ነው፡፡ ነገር ግን ጠራራ ፀሐይ ከሆነ ትንሽ በረድ እስከሚል ድረስ ማዘግየት የበለጠ ይወደዳል፡፡ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል “ሙቀት ከፍተኛ ሲሆን ትንሽ በረድ አድርጋችሁ ዙህርን ስገዱ ከፍተኛ ሙቀት የጀሀነም እንፋሎት ነው፡፡” [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል] የዐስር ሰላት ወቅት የዓስር ወቅት የፀሐይ ጥላ ከአንድ ሰው ቁመት እኩል ከሚሆንበት ሰዓት ጀምሮ ፀሐይ ደብዘዝ እስክትል:: [ሙስሊም ዘግበውታል] የዐስር ሰላት ወቅት የአንድ ነገር ጥላ ከቁመቱ እኩል ከሆነበት ማለትም ከዙህር ማብቂያ ወቅት ጀምሮ ፀሐይ ሊጠልቅ ትንሽ እስከሚቀረው ድረስ ሲሆን ዐስርንም በመጀመሪያው ወቅት መስገድ ሱና ነው፡፡ እንዲያውም መካከለኛይቱ ሰላት በማለት አላህ እንዲህ ሲል የገለፀው ነው፡- ‹‹በሶላቶች (በተለይ) በመካከለኛይቱም ሶላት ላይ ተጠባበቁ፡፡ ታዛዦች ኾናችሁም ለአላህ ቁሙ፡፡› (አል በቀራህ 238) ነብዩም ( ﷺ ) እንዲህ በማለት አዘዋል “የዐስር ሰላትን የተወ ሰው ስራው ይታበስበታል፡፡” [ቡኻሪ ዘግበውታል] በሌላም ሀዲስ እንዲህ ብለዋል “የዐስር ሰላት ያመለጠው ቤተሰቦቹንና ንብረቱን እንዳጣ ነው፡፡” [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታ] የመግሪብ ሰላት ወቅት የመግሪብ ወቅት ፀሐይ ከጠለቀችበት ሰዓት ጀምሮ የሰማይ ደንገዝገዝ እስኪሰወር:: [ሙስሊም ዘግበውታል] የመግሪብ ሰላት ወቅት ፀሐይ ከጠለቀበት ሰዓት ጀምሮ ደንገዝ እስከሚል (ፀሀይ መጥለቂያ ጋር የሚኖረው የሰማይ ቅላት እስከሚሰወር) ሲሆን መግሪብንም በመጀመሪያው ወቅት ላይ መስገድ ሱና ነው፡ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል “ህዝቦቼ መግሪብን ከዋክብት እስኪጠላለፉ ድረስ ካላዘገዩ በመልካም ላይ ናቸው፡፡” [አህመድ አቡዳውድና ሃኪም ዘግበውታል] የዒሻ ሰላት ወቅት የዒሻ ወቅት ደግሞ እስከ እኩለ ለሊት ድረስ [ሙስሊም ዘግበውታል] የዒሻ ሰላት ወቅት ደግሞ እስከ እኩለ ለሊት የሚቆይ ሲሆን ዒሻን ግን አስቸጋሪ ካልሆነ አዘግይቶ በመጨረሻው ወቅት መስገድ ይበልጥ የተወደደ ነው፡፡ ከዒሻ በፊት መተኛትና ከዒሻ በኋላ ደግሞ ወሬ ማውራት የተጠላ ነው:: አቡ በርዛህ ባስተላለፉት ሀዲስ “ነብዩ (ﷺ) ከዒሻ በፊት መተኛትና ከዒሻ በኃላ ማውራት ይጠሉ ነበር::” [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል] ሶላትን ስገዱ ኢማንን ልመዱ ሶላት ያልሰገደ ኢማን ያለመደ እንደ ደረቅ እንጨት ወርዶ ተማገደ
Apr 02, 2024