ለኃያሉ እግዚአብሔር እናቅርብ ምስጋና የሚለውን የሊቀመዘምራን ይልማ ኃይሉ መዝሙር ግጥሙን አስቀምጡልኝ(as a plain text here⬇️)🙏
Mar 30, 2024ለኃያሉ እግዚአብሔር እናቅርብ ምስጋና ለኃያሉ እግዚአብሔር እናቅርብ ምስጋና እሱን ለማመስገን ተፈጥረናልና እርሱን ለማገልገል ተፈጥረናልና (X፪) በተራራዎች ላይ ወፎች ይጮሀሉ በነጎድጏድም ድምፅ ይደነግጣሉ ምንጮችን ለቆላ ንፋስን ለህይወት ስራህ ትክክል ነው ግሩም ነው በእውነት ለኃያሉ እግዚአብሔር እናቅርብ ምስጋና ለኃያሉ እግዚአብሔር እናቅርብ ምስጋና እሱን ለማመስገን ተፈጥረናልና እርሱን ለማገልገል ተፈጥረናልና በተጠሙ ግዜ የበረህ አህዮች ፈጥነው ይሮጣሉ ወደንፁህ ምንጮች ለሰማይ ወፎችም ምግባቸውን ሰጥተህ ሁሉን በየወገኑ ታስተዳድራለህ ለኃያሉ እግዚአብሔር እናቅርብ ምስጋና ለኃያሉ እግዚአብሔር እናቅርብ ምስጋና እሱን ለማመስገን ተፈጥረናልና እርሱን ለማገልገል ተፈጥረናልና የተከልካቸውም የሊባኖስ ዝግቦች ሳርና ቅጠሉ የምድር አበቦች ያመሰግኑሀል በየተፈጥሯቸው ውብና ድንቅ አድርገህ ስለሰራኃቸው ለኃያሉ እግዚአብሔር እናቅርብ ምስጋና ለኃያሉ እግዚአብሔር እናቅርብ ምስጋና እሱን ለማመስገን ተፈጥረናልና እርሱን ለማገልገል ተፈጥረናልና አንተን ተስፋ አድርጎ ይሄ ሁሉ ፍጥረት ምግቡን ይጠብቃል የእጅህን በረከት ፊትህን ስትሰውር ይደነግጣሉ ፍጥረት አትዘንጋን አስታውሰን እያሉ ለኃያሉ እግዚአብሔር እናቅርብ ምስጋና ለኃያሉ እግዚአብሔር እናቅርብ ምስጋና እሱን ለማመስገን ተፈጥረናልና እርሱን ለማገልገል ተፈጥረናልና ጨረቃን ፀሀይን በግዜ አሰልጥነህ አንዱን እያስገባህ አንዱን ታስወጣለህ ሀሩር እና ቁሩን በሚዛን ልለክተህ በየመጠናቸው ትሰዳቸዋለህ ለኃያሉ እግዚአብሔር እናቅርብ ምስጋና ለኃያሉ እግዚአብሔር እናቅርብ ምስጋና እሱን ለማመስገን ተፈጥረናልና እርሱን ለማገልገል ተፈጥረናልና እሱን ለማመስገን ተፈጥረናልና እርሱን ለማገልገል ተፈጥረናልና
Apr 01, 2024