ንግድ ነው ባጭሩ ለምሳሌ መኪና የዛሬ አመት በ700000 ብትገዛ ዛሬ ላይ ስንት ነው 1.1 ያንኑ መኪና 410000 ሺህ ብር አትርፈህ ሸጥከው።ያን ያረገው ደግሞ የተለያዩ ምክንያቶች ናቸው።በቃ ፎሬክስ ላይ ይሄ ምን ሆኖ ይመጣል መኪና/ብር ። በቃ ሁለት ነገሮችን እያወዳደርክ ስትገበይ ፎሬክስ /የውጭ ግብይት(foreign exchange)/ይባላል።ስለዚህ መኪና አሁን ላይ እንዲህ ዋጋው ሊጨምር የቻለበት ምክንያት ለመተንበይ ደግሞ የተለያዩ ቴክኒኮችን ትጠቀማለህ። ለምሳሌ ያህል ዜናዎች፥የመንግስት መግለጫዎችን ወዘተ ያ fundamental analysis ይባላል።ሌላው ደግሞ እንደ moving average,candle sticks ,chart pattern እና ሌሎችም ስትጠቀም technical anaysis ይባላል። ምን መገበያየት እችላለሁ ካልክ ወርቅ፥ገንዘብ ምንዛሬ፥ክሪፕቶ፥ አክሲዮኖችን ና ወዘተ...የforex ገበያዎች ላይ ማግኘት ትችላለህ።forexን ለየት የሚያረገው መኪና ለመግዛት 400000 የለህም እንበል።ስለዚህ እዚህ ጋር የፎሬክስ ደላሎች ይመጣሉ።አንተ 100 ብር ቢኖርህ እንሱ ባዘጋጁት የተለያየ መጠን አራት መቶ ሺህ ብር እንዳለው ሰው ሆነህ ትገበያያለህ ማለት ነው ያም leverage ይባላል።Meta trade፥Binance፥ ወዘተ ለአብነት የሚጠቀሱ ደላሎች ናቸው ።ከዛ ዋጋ ይጨምራል ብለህ ካሰብክ ተገዛ ና ዋጋው ሲጨምር ትሸጣለህ አይ ይረክሳል ካልክ ደግሞ በውድ ሸጠህ በርካሽ ከሚሸጡት ትገዛለህ።አጠቃላይ ሃሳቡ ያ ነው።በዚህ መልስ ላይ በአንተ የተገለጹ ቃላት ላንቺም ይሰራሉ😁
Apr 03, 2024