What is the purpose of መኖር? like For real Endet new yechalachubet sentochachu nachu yemer lebachu be family , Friends , relationship betam bebzu negroch yetsebrachut gen endet newe ቀና belachu rasachun አበርትታችሁ yakoyachut am trying to figure out ma life i don't know anything am in ma late age but still don't know how to act properly in this world especially yeswochen tekyayari behavior melmed ena be okay with it mehon becherash newe yalchalkut leza i distance ma self betam cheye cheye akategn yaw close nachew , fam nachew menmn eyalku lerase excuse eysethu selnber betam kebad honebgn in other side demo saye they don't care at all 🤦♀ Say something eski from ur experience
Mar 29, 2024የገለጽሻቸው ነገሮች ኹሉ የመኖርሽ ማረጋገጫ ማኅተሞች ናቸው። ሰዎች በአንድም በሌላም መልኩ ባሕሪያቸው ይቀያየራል ። ሲርባቸው እና ሲጠግቡ እንኳ ባሕሪያቸው ልዩነት አለው። ብርታትም ድካምም ልክነትም መሳሳትም ገንዘባቸው የኾኑ ፍጥረታት ናቸው ። ሀገራችን ላይ ያሉ ነባራዊ ኹኔታዎች ግን በግሌ በጠበቅኩት መልኩ የሰዎችን ባሕርይ እየቀያየረው ይገኛል ። እኛ ከምናየው ባሻገር በማናየው ኃይል እየተዘወርን ያለበት ጊዜ ነው ። አምሳለ ሲዖል በሰዎች ውስጥ እየተገላበጠች ነው ። ( የከፋው ላይ አልደረስንም በርግጥ ፤ ግን ሩቅ አይደለም ) በቅርቡ ከምታውቂው እየከፋ ይኼዳል ። አንዱ ለመብላት አንዱን መንጠቅ ይጀምራል ። አንዱ በአንዱ ላይ በጠላትነት ይነሳል ። ፈልጎት ብቻ አይደለም ( እንዲገደድ የሚያደርገው ኃይል አለ ) አንቺ እንኳ በዙሪያሽ ያሉትን ሰዎች ተመልክተሽ እንድትሪቂ እያደረገሽ ያለው ይኽ ኃይል ነው። ( ተመልከች ይኽን ኃይል በበጎ ካልተጠቀምሽበት ጥላቻን የሚወልድ ነው ። ነገር ግን ሰዎች ደካሞች ናቸውና ድካማቸውን ተረድተሽ በክፉ ሥራቸው ሳትተባበሪ ግንኙነትሽን በልክ እና በአግባብ ካደረግሽ ይኽን ኃይል የመለወጥ ተፈጥሮአዊ ኃይል አለሽ እንዲኹ በተቃራኒ ጎን የቆመ ሌላ ኃይል ይረዳሻል ። በዚኽ የምትጠቀሚው አንቺ ብቻ ሳትኾኚ በዙሪያሽም ያሉት ናቸው ። ከቻልሽ አኹን ላይ የሰዎችን ክፉ ሥራ አትመልከቺ ። አትስሚም ። ወሬሽ ንግግርሽ ኹሉ በጎ ነገር እንዲኾን ለማድረግ ሞክሪ ፤ አንደበትሽም ክፉን አይናገር ፤ የተጎዱተን እያሰብሽ በአቅምሽ ለመርዳት ጣሪ ። ከምንም በላይ ጸልዪ ! ሰዎች ራሳቸውን እየጠፉ ያሉበትም አንደኛው ምክንያት የሰዎችን ክፋት ከመመልከት እና ሊረዳቸው ካለ ቅዱስ መንፈስ ጋር ሕብረት ለመፍጠር ባለመሞከራቸው በመኾኑ ስለ ሰዎች የክፋት ጉዞ ወይም የባሕርይ ለውጥ መመልከት ትተሽ ወደ ራስሽ ተመልከቺ ። . . . በአጭሩ ይኽ ነው ። በዚኽ ሕይወት አለ ።
Mar 30, 2024