#አንዳንዴ በህይወታችሁ ፍቅርም መውደድም ጥላቻም ያላገኙ ሰውች አጋጥመዋችሁ ያውቃሉ ?? ከነሱ መካከል እኔ አንዱ ነኝ ። ከምማርበት ዩናቨርሲቲ የሚጠላኝ ተማሪ ያለ አይመስለኝም ፣ የሚወደኝም እንዲሁ የለም ፣ የምታፈቅር እንስትም የለችም ። ምናልባትም ከግቢው ካሉት ጠቅላላ ፍጥረቶች የሚያውቁኝ ስሜ የተፃፈበት ኮምፒተሮች ብቻ ይመስሉኛል ። ክላስሜት ሰው የለኝም ፣ዶርም ሜት እንደዚሁ የለኝም ። ስበላ ብቻየን ፣ሳነብ ብቻየን ፣ስኖር ብቻየን ነው ። ስታመም አይዞክ የሚለኝ የለም ፣ሲከፋኝም የሚያፅናናኝ የለም ። እና ከሰው ጋር ለመግባባት ምን ላድርግ ??
Mar 28, 2024Yet gbi neh 🥹 Ene guwadegnah lhon echlalew pls
Mar 30, 2024