ሰላም እንዴት ናችሁ አሁን ያለሁበት ህይወት ደስ አይልም ማለቴ ሱስ ውስጥ ነኝ ከቤተክርስቲያን እርቄያለሁ ነገር ግን አንድ ቀን ይሄ ሁሉ ታሪክ እንደሚሆን አምናለሁ...አሁን ግን social media ላይ በማየው ነገር መንፈሳዊ ቅናት ሊገለኝ ነው ማለቴ ሁሉም ቲክቶከር ምናምን ህይወቱ ተቀይር ነጠላ ለብሰው ገዳም ሲሄዱ ሲያገለግሉ ሳይ በጣም በራሴ እናደዳለሁ እና እራሴን አብዝቼ እጠላዋለሁ...so ምን ላድርግ ምንስ ትመክሩኛላችሁ?
Mar 17, 2024ቲክቶክ እና ቴሌግራም ላይ (አፖስቶሊክ ሰክሰሽን) የሚባሉትን እነ አኬ እና አቡናን ተከተል ከነሱ ስር ወይም ጎን የምታገኛቸውን ሁሉንም ልጆች ፎሎው አድርጋቸው ዲያቆናት አሉ መምህራንም እንደዛው .. ምሳሌ (ዘ-ማሪያም ወይም ቴዲ; ዲ/ን መዝሙረ ያሬድ; ዲያቆን ሕዝቄል;ዳዊት...) ቴሌግራምም ላይ ብዙ ማቴሪያሎች ይለቃሉ በዩቲዩብም አሉ ብዙ ተያያዥ እና ጎን ለጎን ወቀድሞው አቋምህ ስትመጣ ገዳማቱንም አጥቢያዎቹንም በሳምንት አንዴ ሁለቴ ... እያልክ ትመለሳለህ ምንም ራስ መጥላት ምናምን አያስፈልግም ሁላችንም እንወድቃለን እንነሳለን ዋናው መነሳቱ ነው እንጂ ሺ ግዜ መፍረጡ ላይ አይደለም
Mar 17, 2024