Youuu131.5
#other
ሰላም ሰዎች አንድ ቁም ነገር ላወያያችሁ ነበር። እየውላችሁ ክፍል ውስጥ አንድ የምንወደው አካል ጉዳተኛ ጔደኛችን ሞተ እና ከዛ የክፍሉ ተማሪዎች እሱን ለማሰብ በጎ አድራጎት የሚሰራ ቡድን ነገር ለመመስረት አሰብን። ከዛ እኔ እና ሌሎችን 2 የክፍሉ ተማሪዎችን ጉዳዩን እንድናካሄድ መረጡን። ያው 10ኛ ክፍል ነን። ብዙ ጊዜ እንደዚህ አይነት ነገሮች ሲሰምሩ አይታይም። የኔ ጥያቄ ምን መሰላችሁ። ይህንን ቡድን እስከመጨረሻ ድረስ አብሮን እንዲዘልቅ ሁላችንም እንፈልጋለን። ስለዚህ እንዴት ነው አሁን ከ0 ተነስቼ ይሄንን ቡድን ላስተካክል ላንቀሳቅስ የምችለው። እንዴት የምር መሰረቱን ልገንባ? እስቲ ቤተሰብ ሃሳባችሁን አሳውቁኝ። ይመቻችሁ!
Mar 05, 20242 engagements