ሰላም ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ ? ውሸት ምንድን ነው? በቀን ስንቴ ትዋሻላቹ? ለምን ሀቅ ሀቁን አውሩኝ👩🎨
Feb 28, 2024ውሸት የእውነት ተቃራኒ ነው ፡ ሰው በዚ በዚ ምክንያት ብቻ ይዋሻል ብሎ መደምደም አይቻልም ሰው በብዙ ምክንያት ይዋሻል ፡ ሰው በቀን ውሎ ውስጥ እዚ ሄጄ ፣ እንዲ አርጌ ፣ እንትናን አጊንቼ ብሎ ያቅዳል እንጂ ዛሬ ብዙ ላለመዋሸት ልሞክር ብሎ አስቦ የሚኖር ቢኖርና ውሸትን የሚጠየፍ ሰው ካለ ጥቂት ስለሆነ በቀን ውስጥ ሰው ስንቴ እንደሚዋሽ ማወቅ ከባድ ነው ። በእርግጠኝነት የማውቀው ነገር ቢኖር ሰው በአንደበቱ ባይዋሽ በድርጊቱ ይዋሻል ፣ በድርጊቱ ባይዋሽ እራሱን ይዋሻል ይሄ ደግሞ እንትና ውሸታም ነው ወይንም ነች ብሎ መናገርንም ከባድ ያደርገዋል ምክንያቱም በአፉ ሚዋሽ ቢኖር እንኳን በውስጡ እራሱን ላይዋሽ ይችላል ስለዚህ ማነው ውሸታም ?
Feb 29, 2024