መልካችሁን እንደእኔ ጠልታችሁት ታውቃላችሁ? እኔ መልከመልካም/ሸበላ እና አሪፍ አቋም አላቸው ከሚባሉ ወንዶች አንዱ ነኝ ለፍቅር ህይወቴ ግን እንቅፋት ሆኖኛል እኔ በመልኬ ተኩራርቼ ወይ መልኬን ሴቶችን ለማማለል ተጠቅሜበት አላውቅም በፍጹም ነገር ግን ምን ሆነ መሰላችሁ ፍቅረኛዬ ጋር በዚህ ምክንያት ተጣላሁ ብዙ ጊዜ አንተኮ በጣም ቆንጆ ነህ አንዲቷ ሴት እንዳትቀማኝ እፈራለሁ፥ ቆንጆ ወንድኮ የእኔ ነው አይባልም ሴቶች ሁሉ ስለሚወዱት አንዷ ታለምደውና በዛው ይቀራል ትለኛለች በቃ እኔ ለእሷ ያለኝን ንጹህ ፍቅር ለማሳየት ስጥር እሷ በቅናት ቅጥል ነው የምትለው ሰፈር ወይ ኮሌጅ የማውቃቸውን ሴቶች ሰላም ካልኩኝ በቃ ለሳምንት ምናምን ኩርፊያ ነው፤ በጣም የሚያስቀኝ አንድ ቀን እህቴን አታውቃትም እና እህቴን አቅፌ ስሄድ መንገድ ላይ አገኘችኝ እንዴት ከእኔ ውጭ ሴት ታቅፋለህ ብላ ጡፍ አለች ኧረ እህቴ ናት ብል እንዴት ትስማኝ በስተመጨረሻም አንተ በጣም ቆንጆ ነህ በጣም ፈላጊ አለህ ከብዙ ሴቶች አይን ትገባለህ ስለዚህ አብረን መቀጠል አንችልም ብላኝ ተለያየን እኔ ግን በጣም አፈቅራታለሁ ከእሷ ውጭንኳ ሌላ ሴት አይቼ አላውቅም በመልኬንኳ የምኮራ አይነት ወንድ አይደለሁም ግን ልትሰማኝ አልቻለችም ፍቅሬን ልትረዳው አልቻለችም በቃ በዚህ ምክንያት ራሴን ጠላሁት እንደበፊቱ ጂም ገብቼ አላውቅም ራሴን መጠበቅ ሁሉ አስጠልቶኛል
Feb 24, 2024እሺ
Feb 24, 2024