ሰላም ኢትዮያዊያን ቴሌግራምን ስዞራት እናተን አየዋቹ እስቲ አወያዩኝ ታሪኬ ባጭሩ እድሜ ሃያዎቹ መሀል ነው እኔ እንደቀልድ የጀመርኩት የቤቲንግ ቁማር ህይወቴን አበላሽቶታል ድሮ ለመዝናናት ነበር አሁን ላይ ሱስ ብቻ ሳይሆን የግድ መጫወት አለብኝ ምክንያቱም ከቴሌ ብር እና ከጒደኛዬ የተበደርኩት ወደ 140ሺ ብር ደርሶዋል በዚህ ቁማር የተነሳ እንደወንድሜ የማየውን አንድ ጒደኛዬን አጣውት የቴሌብር ብታሰር ነው የሱን ግን ላጣው ስለማልፈልግ የግድ ለመመለስ እጫወታለው አሁን ግን ስራዬም ከሰረ የገንዘብ ምንጬም ቆመ እና ያሉብኝን ብድሮች የመክፈያ ምንም መንገዶች የሉኝም እና አሁን እኔነቴን እራሴን እያጣው ነው አሁን ያለውበት ሁኔታ አስከፊ ነው አሳቤ ሁሉ ይሄን አለም መሰናበት ነው እሱን እኔ ከማጣው ቀድሞ እኔን ይጣኝ በሚል ውስጣዊ አሳብ ጠውጩ ይሄን ነገር ሰዎች ሲያደርጉት በጣም ያናዱኝ ነበር ፈጣሪ የሰጣቸውን ነብስ እራሱ ይንጠቅ እንጂ ለምን ያደርጉታል ብዬ እበሳጭ ነበር አልገባኝም ነበር ልክ እንደኔ መውጫ አተው ይሆን እንደሆነ እሲቲ ቤተሰብ አሳብ ስጡኝ አወያዩኝ!!!
Feb 21, 2024ብሮ በእድሜ እኩያ ብንሆን ነው ብዙ አንራራቅም። እኔም ይሄን ሰሞን እጄ ላይ ትንሽ ብር ነ ይዤ ነበር እና ከቴሌ ብር ተበድሬ ነበር። የቤት ኪራዩን ለመሙላት ሲልም እዳዬንም ለመክል ስል ባለኝ በተረፈው ብር ሙሉ ስመድብበት ነበር(ቤቲንግ) የሚገርምህ ስመድብ ሁሉንም የምበላ ነበር የሚመስለኝ። እና አንድ ቡድን ሲቀረኝ ስሸነፍ ሌላም ሌላም እያልኩ ሙሉ ብሬን ጨረስኩ። እና ምን ልልክ ነው ወንድሜ የቤቲንግ ሱስህን አሁኑኑ አቁም! ነገ፣በኋላ ሳይሆን አሁኑኑ ተው! ብሮ መቼም አትበላቸውም በ5 አመት የቤቲንገግ ለምዴ የተረዳዉት አንድ ነገር ደሞ (ዴቭል) ቁማሩን ከበላው እንደዚ ነው የማደርገው ብለህ በልብህ ከተዘጋጀ መቼም ቁማሩን እንደማያስበላክ ነው። ስለዚህ ተው! ምናልባት የብድርህ ነገር እውነት 140k ከሆነ እና ብዙ ከከበደህ ከ50k members just 20k 50br ብናሳልፍልህ ቢያንስ 100k እናግዝሀለን። ብናግዘውም ባይ ነኝ።
Feb 22, 2024