አስቸኳይ ነዉ!የህክምና ባለሙያዎች ካያችሁት አትለፉኝ። "የደሜ አይነት o -(O Negative)ነው። 2ልጆች ወልጃለሁ 2ቱንም ስወልድ አንታይዲ በ7ወር እና ከወለድኩ ቡሃላ እወስዳለሁ። መጠየቅ የፈለኩት 1አመት በፊት የወሊድ መከላከያ እየዋጥኩ በመሀል ሳላውቅ እርግዝና ተፈጥሮ ነበር እና የጨጋራ ባክቴርያ መርፌ እየወሰድኩ ነበር 1ወር ያልሞላው ፅንስ ወረደ እና ስጠረግ 72 ሰአት አልፎት ነበር እና አንታይዲ አልወሰድኩም ነበር አሁን ከ1አመት ከ5ወር ቡሃላ መውለድ ፈልጌ ውስጤ አንታይዲ መፍጠር እና አለመፍጠሩን ምርምር ታዞልኝ ውጤቱም negativeሆኖ ማርገዝ ትችያለሽ ተብዬ ከዛ እርግዝና ተፈጥራል። 1/15ቀኔ ነው ከላይ በፃፍኩት ምክንያት ወደፊት የከፋ ነገር ልጄ ላይ ያጋጥመኝ ይሆን ደም ማነስ፣ ቢጫ መሆን ከዚህ ጋር ያገናኘው ይሆን? ምንስ ጥንቃቄስ ላድርግ ? ይቅርታ አስረዘምኩት ስለጨነቀኝ ነው ለምትሰጡኝ ምላሽ ከልቤ አመሰግናለሁ።"
Feb 07, 2024ምንም የተለየ ነገር ማድረግ አይጠበቅብሽም ውጤቱ(indirect coombs test) negative ስለሆነ አሁን ላይ የያዝሽው ጽንስ ከሾተላይ ስጋት ውጭ ነው እንደበፊቱ አሁንም 7 ወር ላይና እንደ አስፈላጊነቱ ከወሊድ በኋላ anti D ሙውሰድ ይኖርብሻል። ውርጃው ምንም የተለየ ችግር አልፈጠረብሽም።
Feb 07, 2024