ሰላም። ከእናንተ ምንም ሀጥያት ያልሰራ ሊፈርደኝ ይምጣ! 25ኛ አመቴን እየያዝኩ ነው። ከወጣት ሴቶች ይልቅ በእድሜ የጠኑ ሴቶችን ወደ መውደድ እና እነሱን ለወሲብ ወደ ማሰብ ደረጃ ከገባሁ ይኸው 3ኛ አመቴን እየያዝኩ ነው። ምንም እንኳን እስካሁን ከነሱ ጋር ወሲብ ፈፅሜ ባላውቅም በሀሳብ ደረጃ ግን ከአይምሮዬ ፈፅሜ ማፅዳት አልቻልኩም። ይህ ነገር ልክ እንዳልሆነ ቢገባኝም ቅሉ ከነሱ ግን መራቅ አልቻልኩም። ምናልባት ለዚህ ጥያቄዬ መልስ እኩዮችህን ለመቅረብ ሞክር ሊሆን እንደሚችል መገመት አይከብደኝም። ግን በጭራሽ እነሱ ሊገዙኝ አልቻሉም። በዛ ላይ አብዛኞቹ ኢ-ማቹር ናቸው።(no offense, Mostly not all.)ምን ላድርግ? ተሰቃየው። እተዋለው ብዬ ከሳምንታት እና ወራት ማለፍ ከበደኝ። በዛላይ ክርስትናን እራሱ ካወቅኩ ገና አመት አልሆነኝም እና እሺ ምንድነው ሚሻለኝ? ማወራቸው ሴቶች/ያገቡ አሉኝ ግን መተው እፈልጋለው። ለነሱም ሰላም መስጠት ፈልጋለው ፤ ሰይጣን አለመሆን። ግን አይምሮዬን ሰይጣን እየነዳው እንዴት ላቁም? ዝሙት ከሀጥያቶች ሁሉ መራራ ሀጥያት እንደሆነ እየገባት ነፍሴ ብዙ ፈጣሪዋን ተዳፈረች። ምንድነው ሚሻለኝ? እባካቹ መፍትሄ ሁኑኝ። ነፍሴም አምላኳን እንዴት ላስገዛት ተሰቃየው።😭😭 አንተ ደካማ ሰው ሆይ ማን ነህና እኔ ላይ ለመፍረድ ቸኮልክ? ነገ ምን እንደምትሆንስ በእውነት ታቃለህን?
Jan 17, 2024Brother ፀሎት ብቻ ነው መፍትሄው ፈጣሪ በቃ ካለህ በራስህ ግዜ ያስጠላሀል
Feb 02, 2024