What is the importance of Book of Henok
Oct 05, 2020በትንሽ መፅሀፉ ውስጥ የሚገኙ ነገሮችን ልንገርክ በመጽሓፉ ሄኖክ ከእግዚአብሔር ብዙ ራዕዮች ሲያይ ይናገራል። ደቂቀ ሴት (ትጉሃን) በአመጻቸው ጽናት ከቃየል ልጆች ጋራ አብረው እንዲዋሀዱ ከደብረ ቅዱስ በወረዱበት ጊዜ ሄኖክ እንደ ገሠጻቸው ይላል። የከለሱት ልጆቻቸውም በቁመት አብልጠው ረጃጅሞች እንደተባሉ እነዚህም አባቶቻቸውንና ምድሪቱን እንደ በደሉ ይላል። በሠሩት እጅግ ክፉ ሥራ ምክንያት የጥፋት ውኃ እንደሚደርሰባቸው ፈጽሞም እንደሚያሰምጣቸው የሚል የትንቢትም መጽሓፍ ነው። ይህም ትንቢት ኖህ በኖረበት ዘመን የተፈጸመ እንደነበረ የሚያምኑ ኣሉ። በተጨማሪም ሄኖክ ወደ ሰማያት ተወስዶ የሰማይ ቦታዎችን ያሳዩታል። ከዚህ በላይ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ብዙ ይነበያል፤ ያኔ ጻድቃን ሺ ልጆችን ይወልዳሉና በሰላም በደስታ እንደሚኖሩ የሚል ትንቢት ነው። በዚህ መሠረት የመሢህ፣ የሙታን ትንሣኤ እና የዕለተ ደይን ትንቢቶች መጀመርያ ከሄኖክ ወይም ከአዳም ዘመን ጀምሮ ተገለጹ። መጽሐፉ በሙላቱ የታወቀው በግዕዙ ትርጉም ብቻ ሲሆን፣ የተጻፈበት ቋንቋ፡ በተለይም በኢትዮጵያ መምህራን ዘንድ፡ ግዕዝ መሆኑ ይታመናል። ከዚህም ውጭ አንዳንድ ፍርስራሽ ብራና ቅጂዎች በሙት ባሕር ብራናዎች (በቁምራን ዋሾች) መካከል በአረማይስጥ ቋንቋ በ1950ዎቹ በመገኘታቸው፣ በምዕራባውያን ሊቃውንት ዘንድ መጀመርያ የተቀነባበረበት ልሳን ግዕዝ ሳይሆን አረማይስጥ ይሆናል የሚሉ አሉ። ከዚህም በላይ አንዳንድ የግሪክኛ ወይም የሮማይስጥ ምንባቦች በከፊል ተርፈዋል።
Oct 05, 2020