ሰላም ሰዎች ምን መሰላችሁ ማሰብ ሳልፈልግ ሁላ አስባለሁ ። የማስበውንም አላውቀውም ብቻ አእምሮየ እረፍት የሚባል ነገር የለውም ። ጭራሽ ሳነብማ ይብስብኛል ።በዚህ ችግር ያለፋችሁ ሰዎች ካላችሁ በእናታችሁ መፍትሔ ጠቁሙኝ ። ልብ እንድትሉልኝ የምፈልገው የሀይማኖት ቦታዎች በፍፁም አልቀርም ። ቤተክርስቲያን መሄድ እወዳለሁ ። እስካሁንም ያለሁትም በእግዚአብሔር ቸርነትና በእናቱ በድንግል ማርያም ምልጃ ነው። ከመንፈሳዊ ህይዎቴ ባሻገር ግን አእምሮየን የተቆጣጠሩትን አሉታዊ ሀሳቦች ማጥፋት እንዲሁም አመለካከቴን መቀየር እፈልጋለሁ ። የምትችሉ አግዙኝ ። ስለአመለካከት የተጻፉ የስነ ልቦና መጽሀፍት ካሉ ብትጋብዙኝ ደስ ይለኛል ። ስለተረዳችሁኝ እግዚአብሔር ያክብርልኝ 🙏🙏🙏
Jan 14, 2024@At_Chat_Therapy
Feb 01, 2024