This kinda teyake selemihonbng new orthodox tewahdo be emnet tenkara endehonin enenageraln gn be zefenu industry alen metet normalise tedergwal kidame teteto sekro ehud miaskedis hizb new yalen bezalay ke politics ga lemn tenekaka haymanotu patrialicochachin millionaire nachew be wed mekina ena be bodyguard mitebku ewnetenga kesochachin bado egrachewn eyehedew tsomew yekesulin nberu mn eyadergn new orthodox yihe new bka
Jan 10, 20241) በሐይማኖት ጠንካራ ነኝ ብሎ የሚያስብ ሁሉ ጠንካራ አይደለም። አብዛኛው ሰው ጠንካራ ተብሎ በተለምዶ የሚጠቀሰው ሐይማኖቱን የሚያስክድ ነገር ሲመጣ ስለሚቆጣ እንጂ እውነት በእምነት በምግባር ስለመሠለ አይደለም። 2) ፖለቲካ ግለሰባዊ አመለካከት ነው። ምእመንም ይሁን ዲያቆን አልያም ቄስ ይፋ እንዲያደርግ ባይመከረም የራሱ የግሉ የሆነ ፖለቲካዊ አመለካከት ሊኖረው ይችላል። ያ ማለት ግን ቤተክርስቲያን ዶግማዊ የሆነ የፖለቲካ አመለካከት አላት ማለት አይደለም። 3) አቡነ ማትያስም ሆኑ ከሳችው በፊት ከነበሩት አንድም ፓትርያርክ በሚሊየን የሚቆጠር ተቀማጭ ያለው አንድም የለም። እየተቀስቅክ ያለኸው ሌሎች ጳጳሳትን ከሆነ እነሱም ቢሆን የራሳቸው የሆነ ሚሊየነር የሚያስብላቸው ሀብት የላቸውም። ነገር ግን ብዙ ጊዜ በንሰሐ ልጆቻቸው እና በተለያዩ በጎ አድራጊዎች እቤት እና መኪና የተገዙላቸው አሉ። እነሱም ቢሆኑ የሚያስወርሱ አካል ስለሌላቸው ከሞቱ በኋላ ንብረቱን ለቤተክርስቲያን ይናዘዛሉ። 4) ፓትርያርኩ እና ሊቃነ ጳጳሳት በውድ መኪና የሚሄዱት እነሱ ስለፈለጉ ሳይሆን ፕሮቶኮል ስለሚያስገድዳቸው ነው። የህዝብ ዓይን እንደመሆናቸው ለድኅንነታቸው ሲባል የsecurity standardን የጠበቀ መኪና በቤተክርስቲያንም ሆነ በመንግሥት በግዴታ መልክ ይቀርብላቸዋል። 5) ሊቃነ ጳጳሳት አንድም ወታደራዊ የሆነ የግል ጠባቂ የላቸውም። ነገር ግን ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ እስከዛሬ በቤተክርስቲያኑም ሥርዓት እንደተጻፈው አንድ ሊቀጳጳስ እሱን የሚጠብቅ እና የሚያግዝ ሊቀ-ዲያቆን እና ሊቀ-ካህናት(ቆሞስ) ለራሱ ሊኖረው ይገባል። በዚህም መሠረት ብዙ ጊዜ ፓትርያርኩን እንደ ቦዲጋርድ ከበው ከኋላ እና ከፊት የሚከተሉት አጋዥ ዲያቆናት እንጂ ፈርጣማ ጋርድ አይደሉም። Anyways, ምንም ይሁን ምንም፥ እነዚ ጉዳዮች የኛ ዓላማ መሆን አይገባም። እኛ አይደለም ቀሳውስት እና ጳጳሳትን፤ እራሳችንንም መዳኘት እራሱ ዳገር ስለሆነብን ከዛ ይልቅ የኛ ትኩረት ሊሆን የሚገባው መማር፣ በንሰሐ መታጠብ እና ሥጋወ ደሙን መቀበል ነው።
Jan 17, 2024