Protestantoch genan meche nw yemtakebrut malete kenu mech nw ke ferenjochu ga weys ehud nw?
Jan 06, 2024Okay lemme answer this for you, የክርስቶስ ልደት፣ ሞት እና ትንሣኤው በአመት አንዴ ብቻ ተከብሮ ሌላ ጊዜ የሚረሳ አይደለም። ሁልጊዜ ሊታወስ የሚገባው ነገር ነው ምክንያቱም የክርስቶስ ወደ ምድር መምጣት ለhumanity ትልቅ የምስራች ነው፤ ምክንያቱም ሰው ከእግዚአብሔር የታረቀበት እና የእግዚአብሔር ልጅ ተብሎ የሚጠራበትን access ያገኘበት ነው። ነገር ግን ልደቱን፣ ሞቱን እና ትንሣኤውን እንደ በዓል የማክበር ማንም ግዴታ የለበትም ("እንደ በዓል" አንድ ቀን ወስኖ የማክበር ግዴታ የለበትም)፤ እውነተኛ ክርስቲያን ግን ልደት፣ ሞት እና ትንሣኤውን ሁሌ እያሰበ ያመሰግነዋል። ስለ በዓላት ጳውሎስ እንደዚህ ብሏል: ሮሜ 14 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁵ አንድ ሰው አንዱን ቀን ከሌላው የተሻለ ቅዱስ አድርጎ ይቈጥራል፤ ሌላው ደግሞ ቀኖች ሁሉ እኩል እንደሆኑ ያስባል። እያንዳንዱ የራሱን ውሳኔ ልብ ብሎ ይወስን። ⁶ አንድን ቀን ከሌላው የተለየ አድርጎ የሚያስብ ሰው፣ እንዲህ የሚያደርገው ለጌታ ብሎ ነው፤ ሥጋ የሚበላውም ለጌታ ብሎ ይበላል፤ ለእግዚአብሔር ምስጋና ያቀርባልና። የማይበላም ለጌታ ሲል አይበላም፤ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ያቀርባል። • ይበልጥ ለመረዳት ሙሉ ምዕራፉን አንብቢው። ስለዚህ ማንም ማንንም በበዓላት ምክንያት or በምግብ አይነት judge ማድረግ እንደሌለበት ይናገራል። ምክንያቱም: “የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሰላም፣ በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ሐሤት ነው እንጂ፣ የመብልና የመጠጥ (or የበዓላት) ጒዳይ አይደለም፤” — ሮሜ 14፥17 "Or የበዓላት" የሚለውን እኔ ነኝ የጨመርኩት ከcontextኡ አንጻር። So ጴንጤዎች እነዚህን በዓላት ከኦርቶዶክስ እኩል ስላከበሩ judge ሊደረጉ አይገባም። or ባያከብሩም "ለምን አታከብሩም" መባል የለባቸውም፤ ወይም ደግሞ "የክርስቶስን ልደት መስከረም 29 ላይ እናከብራለን" ብሉም judge ሊደረጉ አይገባም የሚያደርጉትን ሁሉ ለጌታ ብለው እስካደረጉ ድረስ። ⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️ ደሞ Historians እና Bible Scholars የክርስቶስ ልደት ቀን ታህሳስ (December) ውስጥ እንዳልሆነ አረጋግጠዋል። Google it. ☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️
Jan 08, 2024