ሰላም...እነዚህ ጥያቄዎች ለገጣሚዎች ወይም ግጥም ለምትሞክሩ ሰዎች ነው። 1. ግጥም ለናንተ ምንድነው? 2. ግጥም ፅፋችሁ ፅፋችሁ መጨረሻ ግቤ ይህ ነው የምትሉት ነገር ምንድነው? 3. ዘንድሮ "ገጣሚያን" እንደ እንጉዳይ በፈሉበት ዘመን ከነሱ ነጥሮ/ተለይቶ መውጣትን ትፈልጋላችሁ? ምንስ ታደርጋላችሁ ልዩ ለመሆን? 4. የምትወዱትን የራሳችሁን ግጥም አጋሩኝ። አመሰግናለሁ🙏
Jan 06, 20241 መተንፈሻ መንገድ ማስተማሪያ መማሪያና መመራመሪያ 2 ምንም ፣ የትም 3 ሲጀመርም ልዩ ነኝ፣ እኔ እኔን ነኝ 4 በነገራችን ላይ እኔ የምወደው ግጥም የለኝም ስፅፍ ያረካኛል በኃላ ሳነበው normal nw Crazy ስጫወት ካርታውን መዝዤ Crazy ሆንኩልሽ በፍቅርሼ ተይዤ ጫወታው ልብ ነው ካርታውን ጣል ሲሉኝ ፈልጌ አጣሁና ወስዳዋለች አልኩኝ አዎ ወስዳዋለች በጦሩ ቀይራ 5 ሊታስቀጣኝ በፍፁም ሳትራራ ስውል ሳድርማ ጭራሽ ብሶብኛል ስርቃት ናፍቆቷ ስቀርባት ውበቷ ፍዝዝ ያደርገኛል ይበለኝ እንግዲህ የእጄን ነው የሰጠኝ ሌባ ፍት ቁጭብለህ ማን ልብ ጣል አለኝ በድንገት ስጠሩኝ ከሀሳቤ ባትቼ ተረኛ ነህ አሉኝ ስቀው ጓደኞቼ እኔም ነቃ አልኩና ጫወታው ምንድነው ብዬ ጠየቅኴቸው ልቤ እሷጋ ሆኖ አይኔ መች አይቷቸው እነሱም ገርሟቸው flower ነው አሉኝ እኔም አንድ ካርታ አንስቼ እንደ ጣልኩኝ እጄን ከማንሳቴ crazy ተባልኩኝ በድንገት ሁሉም ሰው ከት ብሎ ሲስቅ ቀና ብዬ አይቼ ሁሉን በመደነቅ ለምን ሳቁ ብዬ እያሰላሰልኩኝ የጣልኩትን ካርታ ዝቅ ብዬ አየሁኝ እኔም እንደነሱ ከት ብዬ ሳቅኩኝ Crazy መሆኔን አሁን ገና አወኩኝ ለካስ ያኔ ጣልኩት ነበረ ያንቺን ፎቶ ሌላ አበባ አላቅም የሚበልጥሽ ከቶ ነሀሴ 27 2014 ዓ ም ሃሳብና ነቀፋ እፈልጋለሁ
Jan 07, 2024