አሁን የ fresh ተማሪ ነኝ..እና ግን በጣም ሲበዛ እፈራለሁ ገና ትምህርቱ እንኳን በደንብ ሳይጀመር ብወድቅስ ብዬ እጨነቃለሁ 😔..class ውስጥ መሳቸፍ አይደለም መሳቸፍ ከ5 እንኳን ለመፈቸን በጣጣም እፈራለሁ ምንም በራስ መተማመን ድፍረት ቆራጥነት የሚባሉ ነገሮች የሉኝም ከ ልጅነቴ ጀምሮ ሰነፍ የምባል አይነት ተማሪ ነኝ በራሴ ብጥርም በቃ ትምህርት አይገባኝም ፈተና ጥሩ ውጤት አላመጣም ከkg-12ኛ ክፍል ድረስ አንድም ቀን ጥሩ average አምጥቼ ወይም ከ1-10 እንኳን ወጥቼ አላውቅም😢...እና አሁን ደሞ የunversity ትምህርቴ ላይ ተስፋ የመቁረጥ ስሜት እየተሰማኝ ነው በቃ እኔ መቼም ቤተሰቦቼን በውጤቴ ማስደሰት እንደማልችል ባጠናም እንደማይገኝ ... በቃ እንደዚ ነው የሚሰማኝ.. እና ማለት የሚሰማኝን -ተስፋ የመቁረጥ ስሜት -የበታችነት የአልችልም የፍርሀት... ከነዚህ ስሜቶች ለመላቀቅ በራሴ ጣርኩ video አየሁ ግን በቃ ያው ነኝ ፍርሀቴ በተለይ የተስፍመቁረጥ ስሜቴ ሊለቀኝ አልቻለም.. እና እባካችሁ አ.አ ውስጥ የምታውቁት የስነልቦና አማካሪ ካለ ማለለት አሁን ተማሪ ስለሆንኩ እጄ ላይ ብር የለም በዱቤ የስነልቦና ህክምና የማገኝበት መንገድ ካለ...ወይም እናንተም ምትሉኝ ነገር ካለ እርዱኝ 🙏😪
Jan 01, 2024