DuskParrot26108.5
#education
ሰላም:: እኔ ምለው የ12ኛ ክፍል ማትሪክ AASTU ስለተፈተኑት ተማሪዎች ለምንድነው ዝም የተባለው? የዘንድሮዎቹ ተረኛ እንደሆናቹ አታውቁምን? የምሬን ነው አሁን አንዱን ጓደኛዬን ፌደራሎች ቀጥቅጠው እንደ እባብ መሬት ለመሬት አስኪደውት ጠባሳ በጠባሳ አድርገውታል:: ካላመናችሁ እዛ የተፈተነ የምታውቁት ሰው ጠይቁ:: እጁ በጣም ስለተፋፋቀ ቲሸርት አይለብስም:: ቁስሉ ቢድንም ጠባሳዎቹ ግን አይጠፉም:: ደግሞ እኮ የረበሸውንና ያልረበሸውን ቢለዩ እሺ እነሱ ግን ያገኙትን ሁሉ ዝም ብለው መቀጥቀጥ ነው ስራቸው:: እዛ የነበሩት ፌደራሎች ከልክ በላይ አምባገነን ነበሩ:: እኔ ብቻዬን ምንም አላመጣም ግን ከተባበርን ግን ለውጥ ማምጣት እንችላለን::
Dec 31, 20232 engagements