Wassgud Humans🧍♂🧍♀, What does it mean when they say🎄 "አሲና በል አሲና ገናዬ" 🏑What is አሲና🤔? And What is the whole sentence meaning🧐 what if we dont say "ኢሲና"😄 Explain Me all thing related to this word. Thank You
Dec 29, 2023ከመጽሐፍ ያላገኘውትን የልቤን ላካፍለኽ። አሲና በቀላሉ "አ" አልፋው አ "ጌታ" ማለት ሲሆን "ሲና" ደግሞ የደብር (ተራራ) ስም ነው። "ደብረ ሲና" ይኽም ተራራ ሙሴ ነበልባል እና ሐመልማል በአንድ ተዋህደው የተመለከተበት ነው። አ'ሲና - ይኽም ማለት ጌታ በሲና ለሙሴ እንደተገለጠ ሁሉ በልደቱ በቤተልሔም ለዓለም ተገልጧልና ቤተልሔም ሲናን መሰለች። ከሲና ግን በልጣለች በሲና በምሳሌ በቤተልሔም በኵነት ተገልጦባታልና። በቤተልሔም የተወለደውም ጌታ ቀድሞ በሲና ሙሴን ያነጋገረ መለኮት ነውና። አሲና በል አሲና ገናዬ። ቃለ አብ ሕያው ደብረሲና ዘወረደ። ሥጋኪ ንጹሐ እመ ረሰየ ማኅፈደ። ማርያም ድንግል ዘታቀልሊ ክበደ። ከመ ታጽድቂ ኃጥአን ብኪ መፍቀደ። ወከመ ታጥብቢ ዘከማየ አብደ።
Dec 30, 2023