ንስሃ ስገባ ከአስርቱ ትእዛዛት ዉጪ መናዘዝ ያለብኝ ሌሎች የመጽሃፍ ቅዱስ ህጎች አሉ? ከኦርቶዶክስ እይታ ብቻ ብትመልሱልኝ ደስ ይለኛል
Dec 28, 2023አዎ አሉ ስድስቱ ህግጋተ-ወንጌል 1/ በወንድምህ ላይ በከንቱ አትቆጣ። (ማቴ 5÷22_17 2/ ወደ ሴት አትመልከት በልብህም አታመንዝር። ( ማቴ5÷27) / ሚስትህን ካለ ዝሙት ምክንያት አትፍታ። ( ማቴ 5÷32) 4/ ፈፅመህ አትማል። ማቴ (5_÷34) 5/ ክፉን በክፉ አትመልስ። (ማቴ_ 5÷39) 6 / ጠላትህን ውደድ። ማቴ(5÷45) ከእነዚህም በተጨማሪ ያልተጠቀሱ ስለሚኖሩ ለምሳሌ ጾም ገድፈው ከሆነ እናም የመሳሰሉትን ባጠቃላይ ትክክል የማይመስሉ ነገሮችን በማስታወስ መናዘዝ ነው:: የረሳሁት ይኖር ይሆን ብለውም አይጨነቁ የሚያስታውሱትን ምንም ሳይደብቁ ይናዘዙና ቀኖናዎን ይቀበሉ:: በቀኖና መኃል ድንገት ያልተናዘዙት ኃጥያት ትዝ ካሎት የተሰጦትን ቀኖና ቅድሚያ በመጨረስ በህዋላ ላይ ለንስሓ አባቷ ይናገሩ:: እግዚአብሔር ይርዳዋት:: ያጎደልኩት የተሳሳትኩት ካለ ወንድም እኅቶቼ አርሙኝ::
Dec 29, 2023