እስኪ በደንብ ሙሉ መረጃ ያላችሁ ቤተሰቦች ይህንን ጥያቄዬን ከነ ሙሉ ማስረጃው ጀባ በሉኝ .. መላምት ሊሆን ይችላል መሰለኝ ይብራብኝ ለግዜው 🙏🏾 #ጥያቄዬ ኢትዮጵያ ውስጥ እየኖርን ልጆቻችንን #ሆም_ስኩል ወይም የቤት ውስጥ ትምህርት መስጠት ይቻላል ? ማለትም ከዜሮ ጀምሮ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ በቤት ውስጥ አስተምሮ ሚኒስትሪ እንዲሁም ማትሪክን ያለምንም የትምህርት ቤት ሰርተፍኬትም ሆነ ማስረጃ ልጃችን ብቁ ነው ካልን ፈተናውን እንዲወስድ አድርገን ማረጋገጫ (ትራንስክሪፕት) መቀበል እንችላለን? ስለዚህ ይህንን ፅሁፌን ያነበባችሁ ከላይ በመሀል ቆርጬ ያወጣሁት 2 ምክንያቶች አሉኝ ይህንን ለመጠየቅ ያነሳሳኝ ግን ቦቱ የፊደል ገደብ ስለሰጠኝ ጥያቄው ሲለጠፍ አስገባዋለሁ በሪፕላይ መልክ ...መልስ ያላችሁ ደግም እባካችሁ ጀባ በሉኝ... በዚህ ሀሳብ ለማንፀባረቅ ምትፈልጉ ካላችሁም ደስ ይለኛል እንወያይበታለን አመሰግናልሁ🙏🏾
Dec 27, 2023ስለ ህጋዊነቱ ማውቀው ነገር የለም ግን ልጆች ትምህርት ቤት ሲሄዱ አካዳሚካሊ ያለው ጉዳይ ብቻ ሊታይ ሚገባ አይመስለኝም ፣ ትምህርት ቤት ሲሄዱ ከመንገድ ላይ ጀምሮ እዛ ውስጥ ያለው ህይወት እና ልምድ ከግንዛቤ ሊገባ አይገባውም?
Dec 29, 2023