✍ #ስለ #ማይግሬን #ራስ #ምታት #ማዎቅ #የሚገባዎት #ነገሮች 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ ⏩ #ማይግሬን ከከፍተኛ ራስ ምታት የበለጠ ነው። ይህ የነርቭ በሽታ ለቀናት በአልጋ ላይ ሊያውልዎት የሚችል የሚያዳክም የሚረብሽ ህመም ነው! ማይግሬን ያለባቸው ሰዎች ብዙውን ጊዜ ማጥዎልወል ፣ ማስታወክ እና ብርሃን መጥላትን ይኖራቸዋል። ህመሙ ለሰዓታት ወይም ለቀናት ሊቆይ ይችላል። ⏩ #የማይግሬን ምልክቶች ምንድን ናቸው? የማይግሬን ዋና ምልክት ራስ ምታት ነው። ህመሙ በአንድ ጎን ጀምሮ ወደ ሌላው ሊዞር ይችላል ፣ ወይም የፊትለፊት የግንባር ህመም ፣ የጭንቅላት ጀርባ ላይ ህመም ሊኖር ይችላል ወይም የሙሉ ጭንቅላትን ህመም ሊኖር ይችላል። አንዳንድ ሰዎች ዓይናቸውን ወይም ዓይናቸው አካባቢ ህመም ይሰማቸዋል፡፡ ⏩ #ሌሎች የማይግሬን ራስ ምታት ምልክቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ: 🔺 ለብርሃን ፣ ጫጫታ እና ሽታዎች ስሜታዊነት። 🔺 ማጥዎልወል ፣ ማስመለስ እና የሆድ ህመም። 🔺 የምግብ ፍላጎት መቀነስ 🔺 የሰውነት ሙቀት መሰማት(ላብ) ወይም ቅዝቃዜ (ብርድ ብርድ ማለት) ። 🔺 የቆዳ መገርጣ 🔺 የድካም ስሜት 🔺 መፍዘዝ 🔺 ተቅማጥ (አልፎ አልፎ)። 🔺 ትኩሳት (አልፎ አልፎ)። 🔺 ማይግሬን ለአራት ሰዓታት ያህል ሊቆይ ይችለል ሆኖም ግን ከባድ ማይግሪን በጣም ረዘም ላለ ጊዜ ሊቆይ ይችላል። ⏩ #ህመሙ ሊጀምር ሲል ያሉ ምልክቶች 🔺 ትኩረት ለማድረግ መቸገር 🔺 ከወትሮ በተለየ መነጫነጭ ወይም ድባቴ 🔺 ለማውራትም ሆነ ለማንበብ መቸገር 🔺 እንቅልፍ ማጣት እና በተደጋጋሚ ማዛጋት 🔺 ማጥወልወል 🔺 ድካም 🔺 የምግብ አምሮት 🔺 የጡንቻ ህመም ⏩ #Aura symptoms (ለትንሽ ጊዜ የሚቆይ የስሜት ህዋሳት መዛባት) 🔺 ለሰው የማይሰማ ድምጽ መስማት ወይም ለሰው የማይሸት ሽታ መሽተት 🔺 ጆሮ መጮህ 🔺 ሰውነትን መደንዘዝ እና መንዘር 🔺 የእይታ መዛባት 🔺 ለአጭር ጊዜ የሚቆይ እይታ ማጣት 🔺 በአንድ በኩል የሰውነት መድከም ⏩ #የእራስ ምታት ምልክቶች 🔺 የአንገት ህመም እና መጨምደድ 🔺 ድባቴ እና ስጋት 🔺 ድምጽ ፣ሽታ እና ብርሃን አለመቻል ወይም መጥላት 🔺 የአፍንጫ መታፈን 🔺 እንቅልፍ ማጣት 🔺 ማጥዎልወል እና ማስመለስ ⏩ #ከህመሙ በሆላ የሚኖሩ ነገሮች 🔺 የስሜት ዝቅ ማለት (የድባቴ ስሜት) 🔺 ድካም ⏩ #ማይግሪንን የሚያስነሱ ነገሮች 🔺 1 ምግብ የቆዩ ምግቦች ፤ ጨው የበዛባቸው ምግቦች እና የታሸጉ ምግቦችን መመገብ ለማይግሬን ራስ ምታት መቀስቀስ ምክንያት ናቸው፡፡ ምግብ ሳይመገቡ መቆየትም ማይግሬንን ሊያስነሳ ይችላል፡፡ 🔺 መጠጥ የአልኮል መጠጥ መውሰድ ወይንም ካፌን የበዛባቸውን መጠጦችን መውሰድ የራስ ምታትን ሊቀሰቅስ ይችላል፡፡ 🔺 ምግብ ማጣፈጪያዎች በታሸጉ ምግቦች ውስጥ የሚጨመሩ ምግብ ማጣፈጫዎች እና ምግቦች ሳይበላሹ እንዲቆዩ የሚያደርጉ ኬሚካሎች የማይግሬን ራስ ምታትን ይቀሰቅሳሉ፡፡ 🔺 ጭንቀት በግል ሕይወት ወይንም በሥራ ምክንያት የሚፈጠር ጭንቀት የራስ ምታትን ይቀሰቅሳል፡፡ 🔺 እንቅልፍ ላይ የሚመጡ ለውጦች በቂ እንቅልፍ አለማግኘት ወይንም ከበቂ በላይ እንቅልፍ መተኛት የማይግሬን ራስ ምታትን ሊቀሰቅስ ይችላል፡፡ 🔺 የወር አበባ 🔺 ድካም ከልክ በላይ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መስራት 🔺 ብርሃን የቴሌቭዝን ወይም የኮምፒውተር እና የፀሃይ ጨረር 🔺 በቂ ፈሳሽ አለመውሰድ ⏩ #አጋላጭ ሁኔታዎች 🔺 ይህ አይነት ችግር ቤተሰብ ውስጥ ካለ በዘር የመተላለፍ እድል አለው 🔺 ጾታ ብዙውን ጊዜ ሴቶች ከወንዶች በበለጠ የመጋለጥ እድል አላቸው 🔺 እድሜ 15-55 እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሴቶች 🔺 ሲጋራ ማጨስ ⏩ #የቤት ውስጥ መድሃኒቶች በመባል የሚታወቁ አማራጭ ማይግሬን አያያዝ ዘዴዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ። 🔺 በጨለማ ፣ ጸጥ ባለ ፣ በቀዝቃዛ ክፍል ውስጥ ማረፍ። 🔺 በግንባርዎ ወይም በአንገትዎ ጀርባ ላይ ቀዝቃዛ ነገር ወይም በረዶ መያዝ ህመሙ ሲኖር። (አንዳንድ ሰዎች ሙቀትን ይመርጣሉ ስለዚህ ለብ ያለ ውሃ መያዝም ይችላሉ።) 🔺 የራስ ቆዳዎን ማሸት። 🔺 ዮጋ 🔺 በተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ እራስዎን መጠበቅ። ✅ የዶክተር አለ 8809 የዩቱብ ቻነል
Dec 23, 2023