የአለምን በደል የአለምን በደል የሰውን ግፍ አይቶ ዘጠና ዘጠኙን መላእክቱን ትቶ ጽድቅን ሊመሰርት በደልን አጥፍቶ የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለእኛ የሰማያት ሰማይ የማይችለው ንጉስ ተወልዶ ሲጠመቅ እኛን ለመቀደስ ተራሮች ደንግጠው ዘለሉ በመንፈስ ባሕር ተጨነቀች ጠበባት መሬቱ ዮርዳኖስም ሸሸአልቆመም ከፊቱ እንደተናግረዉ ዳዊት በትንቢቱ ልጁ በዮርዳኖስ ጽድቅን ሲመሰርት መጣ በደመና ሰማያዊው አባት እየመሰከረ የልጁን ጌትነት እንደምናነበው በወንጌል ተፅፎ መንፈስ ቅዱስ ታየ በራሱ ላይ አርፎ በእርግብ ምሳሌ ክንፉን አሰይፎ ባሕር ስትጨነቅ ተራራ ሲዘምር ሰማዩ ሲከፈት ደመና ሲናገር አለም በዛሬው ቀን አየች ልዩ ምሥጢር ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች #share እናድርግ ! #join_share አስተያየት ለመስጠት https://t.me/anduamlak24 አዘጋጅ ገብረ ፃዲቅ ድምፀ ተዋህዶ የንስሀ መዝሙሮች ቻናላችንን ለመቀላቀል https://t.me/ynshawrat