ሰላም ሰዎች እኔ ምላቹ የሰው ልጅ ግን እንዴት ነው የሚኖረው ?የኔ የሚለው ነገር ሁሉ ሲያጣ ነገም ሌላ ቀን ነው ብሎ ከአዲስ ተነስቶ መልሶ የሁኔታዎች አለመመቻቸት የመጀመሪያውን ስህተት መድገም ቆይ ግን ምንድነው እናም የኔም ሁኔታ እንዲህ እየሆነ ነው Please መቼም የማይረሳ ምክርን ምከሩኝ መልስ የሌላቹ ደሞ ምንም አትፃፉ‼Please ‼
Dec 13, 2023ብትወድቅ ብትከፋ የያዘችህ ዓለም ሳታሰናብት መሰናበት በራስ የለም መች መብቴን ብለህ ወደህ ፈቅደህ መጣህባት፤ መብትህ ነው ብላለች አንተን ማኖር መች ጠበባት። ኖሮ ሳይቀምሳት ማን ኑርባት ሞክር አለህ፤ እንዳንተም ሆኖ ኖሮም ዓይቶ እያት ያለህ። ነብሴን ጠላኋት ብለህ የውሸት አትካዳት፤ ለሌላው ሁንና ኖረህ የእውነት አትውደዳት። ግድ ነው ኑሮን መላመድ፤ የኛ አጋር ሆነኻል ዘመድ። ላንተ ሚሆን መቼ አንሶን ቦታ፤ መሄድክን አናይ በቸልታ። መኖርህን ሌሎች ይሻሉ ይፈልጋሉ፤ በህይወት እስካለህ ድረስ ይበረታሉ። የኔ መኖር ነው ላንተም መኖር ያንተም ለኔ፤ ለህይወት አብረን እንዘምር ቁም ከጎኔ። ኑር ባታምንም ላንተ ባይመስልም ለከንቱ አልተፈጠርክም፤ የዛሬው ህይወትህ ባይሞቅም ነገም ካንተ ውጪ አይደምቅም። ድፈር ክረም ኑር በህይወትህ ለሌሎች አቆያት። ፈሪ ነው ያ ሰው ያልሞገተው፤ ሳይገሉት ቀድሞ የሚሞተው ብትወድቅ ብትከፋ የያዘችህ ዓለም ሳታሰናብት መሰናበት በራስ የለም መች መብቴን ብለህ ወደህ ፈቅደህ መጣህባት፤ መብትህ ነው ብላለች አንተን ማኖር መች ጠበባት። ኖሮ ሳይቀምሳት ማን ኑርባት ሞክር አለህ፤ እንዳንተም ሆኖ ኖሮም ዓይቶ እያት ያለህ። ነብሴን ጠላኋት ብለህ የውሸት አትካዳት፤ ለሌላው ሁንና ኖረህ የእውነት አትውደዳት። ግድ ነው ኑሮን መላመድ፤ ከኛ ጋር ደፍረህ ተራመድ። መቅረትክን አናየውም በደስታ፤ በርትተህ እኛንም አበርታ። መኖርህን ሌሎች ይሻሉ ይፈልጋሉ፤ በህይወት እስካለህ ድረስ ይበረታሉ። የኔ መኖር ነው ላንተም መኖር ያንተም ለኔ፤ ለህይወት አብረን እንዘምር ቁም ከጎኔ። ኑር ባታምንም ላንተ ባይመስልም ለከንቱ አልተፈጠርክም፤ የዛሬው ህይወትህ ባይሞቅም ነገም ካንተ ውጪ አይደምቅም። ድፈር ክረም ኑር በህይወትህ አቆያት። ፈሪ ነው ያ ሰው ያልሞገተው፤ ሳይገሉት ቀድሞ የሚሞተው መኖርህን ሌሎች ይሻሉ ይፈልጋሉ፤ በህይወት እስካለህ ድረስ ይበረታሉ። የኔ መኖር ነው ላንተም መኖር ያንተም ለኔ፤ ለህይወት አብረን እንዘምር ቁም ከጎኔ። ግጥም ዜማና ሙዚቃ ቅንብር :- ኤልያስ መልካ ድምፅ ዘሪቱ ከበደ፣ አብነት አጎናፍር፣ ጆኒ ራጋ
Dec 14, 2023