ኧረ በማርያም ምን ላድርግ ሁሌ የማየው ህልም የእውነት ይሆናል ጨነቀኝ እኮ ደሞ ምንም ጥሩ ነገር አይታየኝም መጥፎ ነገር ብቻ የማየው በዚህ ምክንያት መኖር ሁላ ያስጠላኛል ምን ማድረግ ነው ያለብኝ ቆይ ደሞ በህልም ብቻ ሳይሆን እንዲሁም የማስበው ነገር ሁሉ ይደርሳል መኖር እየፈራሁ ነው ለሰዎች ሳማክር ከምንም አይቆጥሩኝም። እባካችሁ እርዱኝ
Dec 09, 2023የፈሩት ይደርሳል ፤ የጠሉት ይወርሳል ! በጎ ተመኝ በጎም አስብ በጎ ታገኛለኽ። በጎ ባታገኝ እንኳ ለበጎ ነው ብለኽ ፈጣሪን አመስገን ነገሩን ወደ በጎ ይቀይርልኻል። 1. ሕልምን ያመነ ጉም የዘገነ ይባላል። አንድም ሕልም ከማይታየው ዓለም እንደመሆኑ ወደሚታየው ዓለም ከመገለጹ በፊት ማስጠንቀቂያ ነውና በጸሎት ከመትጋት ጀምር። በአጭሩ።
Dec 10, 2023