Hey guys, zare kelbachihu endtmelsulgn new yemfelgew yesew lj lidnbet hywetun lilewtbet kehulum yeteshalew menged mndn new blachihu tasbalachihu enante yetekebelachihut flsfna mndn new?
5 votes
Hey guys, zare kelbachihu endtmelsulgn new yemfelgew yesew lj lidnbet hywetun lilewtbet kehulum yeteshalew menged mndn new blachihu tasbalachihu enante yetekebelachihut flsfna mndn new?
5 votes
ይህንን የመረጥኩት አብዛኞቹን ነቅፌ ሳይሆን ምርጫህ ውስጥ አዘር የሚል ስለሌለ እና ከምርጫዎችህ ቢያንስ 4ቱ ማለትም (ስራ፣ደግነት(በጎአድራጎት)፣ ትምህትና ፍቅር በዚህኛው ስለሚጠቃለል ለእኔ እና ደግሞ ስቲል ገና ህይወቴ ስላልተቋጨ እየተፍጨረጨርኩ ስለሆነ ገና ያላወኳቸው አውቄም ራሱ በህይወቴ ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ ያልቻልኳቸው ብዙ ነገሮች ስላሉ ገና ስለሚቀጥልም በየናኖ ሰከንዱ ውጣ ውረድ መሸነፍ መነሳት እንደገና መሰናከሌ ስለሚቀጥል የመጨረሻው አማራጭንም ስለሚያስኬድ ነው .... ስለዚህ ይህን ካልኩ ዘንዳ የሌላው መለወጫ/መዳኛ የእኔ ሊሆን እንደማይችል ማመን ቀዳሚው ተግባር ነው ነገር ግን እንደ ሰብአዊ ፍጡር እሚያመሳስሉን ነገሮች ይኖራሉ ስለዚህ ለሁሉም መጀመሪያ ፈጣሪን መፍራት እንደሆነ እመን እሱን ስታምን የከበደ ሚካኤል (ፅድቅና ኹናኔ ቢኖርም ባይኖርም፥ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም) ምትለዋን ወርቅ ስንኝ በህይወትህ ውስጥ አስገባው :: በዚህ ከተስማማን ዘንዳ ሀይማኖት ብዙ አለ አለም ላይ አብዛኞቹ ፕሪች ሚያደርጉት "በጎነትን ሩህሩህነትን መሬት ሆኖ መኖርን ለምድራዊ ቁስ አለመገዛትን ነው ሌላው ሚለያዩን ነገሮች ትርፍ ስፒሪቿል ክንዋኔዎች እና ቴክኒኮች ናቸው :: እንደ አንድ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኝ የእኔ ሀይማኖት ከሁሉም እንደሚበልጥ እና በዚህ ዶግማና ቀኖና አባቶቼ በነደፉልኝ መንገድ አቅሙን እና ብርታቱን ሰቶኝ በህይወቴ ሙሉውን ባይሆን እንኳን ዋንኞቹን ተግባራዊ ካደረኩ መግስተ ሰማይን እንደምወርስ አምናለሁ.. ይህንን ስልህ ሌላው ሀይማኖት ከእኔ ያንሳል ወይም መንግስተ ሰማያትን ሳይሆን ሲኦልን ነው ሚወርሱት ለማለትም አልደፍርም ምክንያቱም ከላይ የጠቀስኩልህ እሚያመሳስሉንን ነገሮች በህይወት ዘመናችን ከተገበርን አንዳችን በሌላኛችን ሀይማኖት ውስጥ እየኖርን መሆኑን እረዳለሁ (ለምሳሌ መግደል ሀጢያት እንደሆነ አብዛኛው ሀይማኖት ያስተምራል ስለዚህ ባለመግደል የፈጣሪያችንን ትእዛዝ እያከበርን ነው ማለት ነው) በተቃራኒው አትብሉ ሚባሉ ነገሮች ይለያያሉ በየሀይማኖቱ ስለዚህ ፈጣሪ በጠራኝ ኢቺ ሀይማኖቴ ውስጥ እየኖርኩ እነዛን ክልክል ነገሮች ከተመገብኩ አንድም ሀይማኖቴን እየከዳኃት ነው ለዛም ሀጢያተኛ እባላለሁ ነገር ግን የሌላ ሀይማኖት ተከታይ እኔ ሀይማኖት ውስጥ የተከለከለ እሱ ጋር ግን የተፈቀደ መሆኑን አምኖ ቢመገብ በራሱ ሀይማኖት የመፅደቅ እድል ይኖረው ይሆናል ነገር ግን የሱን ሀይማኖት በእኔ ሀይማኖት መገምገም በራሱ ለእኔ ሀጢያት ነው ምክንያቱ ፈራጅ ገምጋሚ አንድ አምላክ ስለሆነ ... በዚህ መልኩ ህይወትህ ላይ ሚፈጠሩ የእምነት ግጭቶችን አቻችለህ ለማለፍ ከሞከርክ እና በማያገባህ እምነት ውስጥ ጣልቃ ሳትገባ ሰውን እንደ ሰብአዊነቱ ሀይማኖትህ በሚያዘው መጠን ተቀብለህ ከኖርክ ይመስለኛል ህይወት ቀላል ባትሆንም ህሊናህ ግን ከወቀሳ የፀዳ ይሆናል ባይ ነኝ:: ስለዚህም (ኮንፊሺዝም/ሺሽቶሲዝም /ቡዲዝም... እና መሰል ካደክበት ሩቅ የሆኑ እምነቶች ውስጥ ጣልቃ እየገባህ ባትተራመስ እመርጣለሁ ማወቁ እንደእውቀት መልካም ቢሆንም ያንን ወደራስህ ህይወት አምጥተህ ያለህን ከቤተሰብ ከህብረተሰብ ብሎም ከሀገር የተቀበልከውን ሀይማኖት ላይ እየበረዝክ ምትጠቀም ከሆነ እመነኝ ⚠️ት.ጨ.ል.ላ.ለ.ህ⚠️) ለምሳሌ የወረስከው እምነት ኦርቶዶክስ ከሆነ እመነኝ ተነክቶ ያላለቁ እውቀቶች እና የአባቶቻችን ምክር ገድል እውቀት ምርምር ከበቂ በላይ ይገኛል ማየቱ ካልጋረደብህ በቀር) እስልምናንም ካየኸው ብዙ ተነክተው ያላለቁ ራስህን ለጥሩ ማንነት ሚያበቁ ትምህርቶች እንደሚኖሩት አምናለሁ ምክንያቱም አብዛኞቹ ወዳጆቼን ሳስተውል የተረጋጋ ህይወት ፀሎት እና ደግነትን ስለማይባቸው የዛ እምነት ተከታዮችን... ስለዚህ ይህንን ሁሉ አንብበህ ሳትሰለች እዚህ ከደረስክ ዘንዳ እኔ ባልተገብራቸውም በሌሎች ተተግብረው ለውጥ ያየሁባቸውን ጥቂት ነገሮች ጀባ ልበልህ... 👉🏾 አንደኛ ለሀይማኖትህ ከዛም ለቤተሰብህ ከዛም ለሀገርህ ሁሉ ነገርህን ሳትሰስት ለግስ 👉🏾ሁለተኛ በፍፁም ለቁስ አካል ተገዢ አትሁን የፈለገውን ያኽል ድሀ ሆነህ ኑር ላንተ ያለው ለአጭሯ ስጋዊ ህይወትህ የምትሆነዋን አታጣም 👉🏾የሀይማኖት ክርክር እና ሙግት ውስጥ አትግባ ብትችል ተሟጋቾችህን ወደ ሀይማኖት መምህራንላካቸው (አንተ የሀይማኖት መምህር ካልሆንክ በቀር) 👉🏾በእቅድ ኑር ስለነገ አቅድ ስለየዛሬ አመት አቅድ ስለ የዛሬ 5 አመት አቅድ አምስቱን አመት እቅድህን ገምግመህ ያላሳካኸው ነገር ከገጠመህ ምናልባትም ችግሩ ከእቅድህ ሊሆን ስለሚችል እቅድህን ቀይረው ያ ላንተ የተፈጠረ ላይሆን ስለሚችል ችክ አትበል በተረፈ በተቻለህ አቅም ደስታን ሚፈጥሩልህን ነገሮች (ከሀይማኖትህ/ከባህልህ/ከህሊናህ) ሳትርቅ ተግብራቸው ብዙውን ግዜ ለእኔ ሰውን በቀላል ጉዳዮች ያለምንም ተጨማሪ አፀፋዊ ምላሽ መርዳት ደስ ይለኛል ባለህ አቅም አድርገው ውስጣዊ ሰላምና ነፃ ህሊና ታገኝበታለህ:: አመሰግናለሁ ለንባብህ
Dec 02, 2023It is better All of them bro
Dec 02, 2023I would choose stoicism cause it's about peace n love but above all it teaches bout inner peace n being in peace wiz everyone n everything surrounding u it's the same as christianity
Dec 02, 2023That's really obvious
Dec 14, 2023I think work, virtue, love and education can be included under stoicism. At the end of the day, I don't think you need a set of rules to lead your life. Nobody is perfect in this world. Just try to do what is good and that doesn't hurt anybody else. I like the verse "Do unto others as you would like them to do to you". In other words, treat all like you want to be treated, and more than that treat all as God has treated you.
Dec 02, 2023