Best Things to do before 20's list mazegajet felge give me some idea's to add on my bucket list Eski tell me things you are proud of doing in your teenage years & Things you regret not doing. Book recommendation,self devlop or discipline tips. lihone ychelal please share eski would like to hear it😁 Am 19 F what things i should do on my age except(drinking,s**,dating & stuff) Ps.Don't pass if you're above 19 share ur ideas thanks love y'all❤️
Dec 01, 2023ሴትነትሽን ጠብቂ እስክታገቢ ድረስ Sex አታድርጊ፣ መፅሀፍ ቅዱስ በየቀኑ አንድ ቻፕተር አንብቢ፣ መፅሀፎች አንብቢ፣ የምትወጂዉን Hobby በደንብ አጠንክሪዉ በትምህርትም ቢሆን፣ ትንሽ ቢዝነስ ጀምሪ፣ Skill የተባሉ ከ1ወር እስከ 6 ወር የሚፈጁ ኮርሶች ከዋናዉ ትምህርትሽ በተጨማሪ በዕረፍት ሰአትሽ ተማሪ፣ ከሀገር ዉጭ ካሉ ባለሙያዎች በምትፈልጊዉ ነገር ዙሪያ ቻት አድርጊ ኔትዎርክ አድርጊ አለም ጥላሽ አትሄድም፣ ዉበትሽን ካሁኑ ጠብቂ፣ የራሴ የምትይዉ ነገር እስኪኖርሽ ብዙ ነገር ሞክሪ አንዱ ላይ እንድታርፊ ያግዝሻል፣ ጓደኞች አታብዢ እነሱም አላማቸዉ እሩቅ የሆነ ቢሆኑ ይመረጣል፣ ደፋር ሁኚ ድንበርሽን አታስደፍሪ ብዙዎች ሰባብረዉ ይጥሉሻል። No ማለት ገገማ መሆን አይደለም፣ ምንም ነገር ስትሰሪ እስከ ጥግ ጥንቅቅ አርገሽ ስሪ ተማሪ ከሆንሽ ጎበዝ ተማሪ ሁኚ ጊዜሽን ዝም ብለሽ አትግደይ በስንፍና፣ ኮንፊደንስሽ ላይ ስሪ ሁሉም ሰዉ እንዲወድሽ አጠብቂ፣ ትልልቅ ህልሞች አልሚ አትስነፊ፣ የወንድ ጓደኛ ከያዝሽ እስከመጋባት አላማ ያለዉ ጎበዝ ወንድ ምረጪ…ስታይል ያለዉ ምናምን ሳይሆን ትልቅ ህልም ያለዉ ተያይዛችሁ የምታድጉ መሆን አለበት። የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ሁሌም ካሁኑ ጀምረሽ አድርጊዉ። ደስተኛ ሰዉ ያደርጋል። ካለን እዉቀት፣ ጉልበት እና ገንዘብ ለሌላዉ ማካፈል ግድ ነዉ። እንደ እህቶቼ ነዉ የመከርኩሽ እኔ 31 አመቴ ነዉ በህይወቴ የሚቆጨኝ አንድ ቀን የለም ደስተኛ ስኬታማ ሴት ነኝ። ላንቺም ይጠቅምሻል ብዬ ነዉ።
Dec 02, 2023