እንዳታልፋኝ አባካቹ! ሰላም እንዴት ናቹ ተማሪ ነኝ እራሴን ለመደገፍ ብዬ እቃ እየገዛው አትርፌ እሸጣለው የዛሬ ሁለት ሳምንት አካባቢ አራት ስልክ Samsung S3 በቅናሽ አለ ተብዬ አትርፌ ለመሸጥ እያንዳንዱን በ 2700 ገዛሁ በወቅቱ እጄላይ የነበረው 1500 ብር ብቻ ስለነበር ሸጬ እመልሳለው በሚል 9300 አካባቢ ከሰው ተበደርኩ ስልኮቹን አምጥቼ ለቅርብ ሰው ሸጥኳቸው ግን አራቱም በነጋታው ተመለሱ ሁሉም የባትሪ ችግር ያለባቸውና repacked የተደረጉ እንደሆነ ተረዳሁ ይባስ ብሎ አንደኛው power button ወደ ውስጥ ገባ... ግራ ተጋብቻለው በዚ በኩል ልጁ(አበዳሪው) ገንዘቤን አምጣ ብሎ ሊገለኝ የቀረው ነገር የለም ...ስልኮቹን ለማያቅ ሰው እንዳልሸጥ ደሞ ህሊናዬን መሸጥ ሆነብኝ ምን ላርግ ወገኖች? እንቅልፍ ካጣው ይኸው 2 ተኛ ሳምንቴ
Nov 30, 2023ለመሸጥ ሞክር አንዳንዴ በህይወት ጨካኝ መሆን አለብህ ጨካኝ ስልህ ከነብስ ጋር የማይገናኝ ነገር 🙌🙌🙌
Dec 01, 2023