ነገ 22ዓመት ልደቴ ነዉ ጥሩ ተስፋ ሚሰጥ ንግግር ንገሩኝ ተስፋ አጥቻለዉ በዚች አጭር ጊዜ 😔🙌
Nov 29, 2023[ የዘገያችሁ ከመሰላችሁ .... ገና ናችሁ] አንዳንድ ሰው በ24 አመቱ ተመርቆ ስራ ለማግኘት 6 አመት ሊፈጅበት ይችላል አንዳንዱ በ24 አመቱ የድርጅት ስራ አስኪያጅ ሆኖ በ30 አመቱ ሊሞት ይችላል ሌላው ስራ አስኪያጅ ለመሆን የ26 አመት ልምድ አስፈልጎት 80 አመቱ ኖሮ ይሆናል አንዳንዱ በ49 አመቱ ገና ላጤ ሆኖ ህይወቱን ለመቀየር ሲታገል የትምህርት ቤት ጓደኛው የልጅ ልጅ አይቶ አያት ለመሆን በቅቶ ይሆናል ኦባማ በ55 አመቱ ጡረታ ሲወጣ ትራምፕ በ70 ባይደን በ77 አመታቸው ነው ፕሬዝዳንት የሆኑት በዚህች ምድር ላይ ሁሉም የራሱ ጊዜ አለው ሰዎች የቀደሙህ ወይም አንተ የዘገየህ ሊመስልህ ይችላል። አንተ ወደፊት ገስግሰህ ሌላው ወደኋላ የቀረ መስሎ ሊታይህም ይችላል። እውነታው ግን ሁሉም ሰው በራሱ ጊዜ፣ በራሱ ፍጥነት እየሮጠ ነው። አንተም በራስህ እነሱም በራሳቸው ጊዜ ከተፃፈላቸው ቦታ አይቀሩም። ልጅ ለመውለድ፤ ገንዘብ ለመያዝ፤ ትዳር ለመመስረት፤ አገራችሁ ለመግባት፤ ተምሮ ለመመረቅ፤ ለመዝናናት ...... የዘገየህ ለመሰለህ .... አልዘገየህም፤ ከማንም አትቀድምም፤ በራስህ ጊዜ ላይ ነህ !!
Nov 30, 2023