#religion I have a question for our protestant families....እየሱስ ክርስቶስ ከሰየ ሰማያት ወርዶ አለሙን ሁሉ ለማዳን ተሰቅሏል ...በዚህ ሁሉም ክርስቲያን ያምናል።...ታዲያ የእኔ ጥያቄ ለምንድነው ሁሌ ኢየሱስን የግል አዳኝ አድርገህ ተቀብለሃል የምትሉት ?...መፅሐፍ ቅዱሳዊ መሰረትስ አላችሁ?...የግል አዳኝ የሚል ቃል እንድታሳዩኝ ነው የምፈልገው።
Nov 19, 2023ይህ ጌታን መቀበል? ጌታን መቀበል የተወሳሰበ የስነ መለኮት ቃል አይደለም። ፍቺና ፈቺ የሚፈልግ ጥልቅ አስተምህሮም አይደለም። ይህንን ትልቅ እና ድንቅ እውነት እግዚአብሔር የተወሳሰበ አድርጎ አላቀረበም። በጣም ግልጽ፥ በጣም ቀላል ነው። ሁላችንም ሰጥተንም ተቀብለንም እናውቃለን። ይህ መስጠትና መቀበል ከሰው ፍጥረት ጀምሮ የኖረ ልምድ ነው። በመስጠትና በመቀበል ውስጥ ሰጪ አለ፤ ተቀባይ አለ፤ ስጦታ ደግሞ አለ። ይህንን ጌታን መቀበል የሚለውን እውነት የሚያስረዱን ሁለት ጥቅሶች እንመልከት። የመጀመሪያው፥ የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም። ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው። የሚለው ነው፤ ዮሐ. 1፥11-12። ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ የመጣ አምላክ ነው። ሙሉ አምላክ ሆኖ ከአምላክነቱ ምንም ሳይቀነስ ፍጹም ሰው ሆኖ የመጣ ነው። በሥጋ መምጣት የኖረበት ምክንያት ሊቤዠን ወይም ቤዛ ለመሆን ነው። ቤዛ ማለት ምትክ ማለት ነው። በምትካችን ሊሞት፥ ኃጢአታችንን ሊወስድ ማለት ነው። ሳይሞት ኃጢአታችንን ሊወስድ ወይም ሊደመስስ አይችልም ነበር ወይ? ኃጢአት እንዲህ በቀላሉ ድምስስ የሚል ነገር አይደለም። ኃጢአት ደመወዝ አለው፤ ደመወዙም ሞት ነው፤ ሮሜ 6፥23። ኃጢአት የእግዚአብሔር ተቃራኒ ባህርይ ነውና ኃጢአት ሁሉ ሕይወትን ይጠይቃል። ጌታችን ሁሉን መስፈርት የሚያሟላ ቤዛ ነው። ይህንን ሆኖ ነው ወደ ወገኖቹ የመጣው። የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም። ሰው ሆኖ መምጣት ከኖረበት ወደ አንድ ወገን መምጣት አለበት። ያ ወገን ማንም ሊሆን ይችላል። ያንን ወገን ከአብርሃም ወገን እንዲሆን እግዚአብሔር መረጠ። ተስፋ ሰጠ። በትንቢት ተናገረ፤ ሕጻን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል እያሉ ነቢያት ተናገሩ። ተሰጥቶናል ሲሉ ስጦታ መሆኑን መናገራቸው ነው። ስጦታ ከሆነ ይህ ስጦታ የሚቀበሉት ስጦታ ነው። ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው። የሚለው ነው። ስጦታ ዋጋ የተከፈለበት፥ ግን ተቀባዩ ያልከፈለበት፤ እንዲቀበሉት የተገባ ግን ግዴታ የሌለበት የፈቃድ ነገር ነው። ይህ ነው መቀበል። መቀበል መውሰድና የራስ ማድረግ ነው። ስጦታው ዕቃ ከሆነ ወስዶ መጠቀሚያ ማድረግ ነው። ስጦታው ጌጥ ከሆነ ተቀብሎ ማጌጥ ነው። ስጦታው ጌታ ከሆነ ተቀብሎ ጌታ ማድረግ ነው። ክርስቶስን ጌታ አድርጎ መቀበል ማለት በራስ ላይ ጌታ እንዲሆን መፍቀድ ነው። ይህ 'የግል አዳኝ' የተባለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም። ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ አሳብ ነው። የግል ማለት የራስ ማለት ነው። የግል አዳኝ አድርጎ መቀበል ሲባል ተቀባዩ ራሱ በውሳኔው የሚቀበለው መሆኑን መናገሩ ነው። ወላጆቼ ስለ እኔ ጌታን አይቀበሉልኝም። ፈቃዴ የለበትማ! ይልቅስ ከዚያ በኋላ ቃሉን በማስተማር፥ ክርስቶስን በማሳየት ተግተው ኖሮ ቢሆን መልካም ነበር። ያንንም እንኳ አድርገው እኔ በራሴ ውሳኔ፥ በራሴ ፈቃድ ጌታን ጌታዬ አድርጌ ካልተቀበልኩ አይሆንም። ምክንያቱም ይህ የጌታና የተከታይ ግንኙነት ነው። በግድ ከሆነ ፈቃድ የለበትም። ተገድጄ ነው የምከተለው። ፈቃድ ደግሞ እግዚአብሔር ማንንም ሳይለይ ለሰው ልጆች ሁሉ የሰጠው ድንቅ ስጦታ ነው። ለዚህ ነው የግል አዳኝ የተባለው። ውሳኔው ማንም ለማንም የማያደርገው የግልና የፈቃድ ውሳኔ ስለሆነ ነው። አንድ ምሳሌ ልጥቀስልህ የሆነ ስጦታ አኔ ይዤ ብመጣ አንተ/አንቺ ለመቀበል ፍቃድሽ ያስፈልገኛል ስጦታውን ሰለፈለለከው/ሽው ብቻ የራስህ/ሽ አታረጊውም መቀበል ይኖርብሀል/ሻል.... ሁለተኛው፥ እንግዲህ ጌታን ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ ተቀበላችሁት በእርሱ ተመላለሱ። የሚል ቃል ነው፤ ቆላ. 2፥6። ጌታን ስንቀበል የተቀበልነው እንደ ጌጥ ወይም እንደ መብል ሳይሆን እንደ ጌታ ነው። ስለዚህ በኛ ላይ በፈቃዳችን የሆነ ጌትነቱን ነው የተቀበልነው። ባንቀበለውም እርሱ ጌታ ነው። አንድ ቀን ጉልበት ሁሉ ለእርሱ ይንበረከካል፤ መላስ ሁሉ ለአብ ክብር ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ ይመሰክራል። ይህ እውነት ነው። ግን ጌትነቱን መቀበል በኛ ላይ ጌታ፥ አለቃ፥ አዛዥ፥ ባለ ሙሉ ሥልጣን፥ ንጉሥ፥ አምላክ እንዲሆን ፈቅደን መቀበላችን ነው።
Nov 19, 2023