Selam sewoch ke guadegnoche ga theatre bet mehed feligen nbr ena suggest adrgun eski arif theater ena theater bet weekend lay
Nov 16, 2023በነፃ! የኖርዲክ ብላክ ቲያትር:- ማያ አንጀሉ ደራሲት፣ ተዋናይት፣ የስክሪፕት ጸሐፊ፣ ዳንሰኛ፣ ገጣሚት፣ የመብት ተሟጋች ፤ በርካታ የህይወት ታሪኮችን፣ ድርሰቶችን፣ በርካታ የግጥም መጽሃፎችን ያሳተመች ፡ከ50 አመታት በላይ የታዩ የትያትር፣ ፊልሞች እና የቴሌቭዥን ትርኢቶች ላይ የቆየች፣ ከ50 በላይ የክብር ዲግሪዎችን ያገኘች …ኧረ ይህች ሴት ማነች? …አርአያነቷስ ምድነው? የኖርዲክ ብላክ ቲያትር በአለም ላይ እየተዘዋወረ ትምህርት ተኮር የሆኑ ትያትሮችን በማሳየት ይታወቃል፡፡ ታዋቂ አርቲስቶች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በኖርዌይ እና በኢትዮጵያ መካከል የሚደረገውን የባህል ልውውጥ እና ግንኙነት ከፍ ከማድረግ ባሻገር በኪነጥበብ ተዝናኖት ውስጥ ፈታ ዘና እያልን ቁምነገርን እንድንሰንቅ በማያ አንጀሎ ህይወት ላይ ያተኮረ "Black women rising " የተሰኘው ቴአትር በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር አርብ ህዳር 7ቀን 2016 ዓ/ም ከምሽቱ 11፡30 ጀምሮ ይቀርባል፡፡ የኪነጥበብ ባለሞያዎች፣ቤተሰቦች፣የኪነጥበብ አፍቃሪያን በሙሉ በነጻ ተጋብዛችኋል፡፡ ከጠንካራዋ ከማያ አንጀሎ ታሪክ ምን ይጨልፉና ለቤተሰብዎ ያቀብሉ ይሆን ? "ቴአትር የእርስዎ የራስዎ የህይወትዎ ገጽ! ይመልከቱ!" የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ህዝብ ግንኙነት በብስራት ኤፍ ኤም 101.1 ዘወትር ሀሙስ ከምሽቱ 3 ሰዓት እስከ 6 ሰዓት የሚተላለፍ የሬዲዮ ፕሮግራም ነው፡፡ Tg accunt @stmnewjobs gebth eyew
Nov 18, 2023