urgent AAU extension yetemezegebachu ye temehret masreja yalut mn mn new ena originalun new weys copy Amesegenalew🙏
Nov 16, 20238 10 12 9-12 transcript Copy nw ..for more use aau official portal
Nov 16, 2023urgent AAU extension yetemezegebachu ye temehret masreja yalut mn mn new ena originalun new weys copy Amesegenalew🙏
Nov 16, 20238 10 12 9-12 transcript Copy nw ..for more use aau official portal
Nov 16, 2023እኔ ያደረኩት እና የተቀበሉኝ websiteኡ ላይ ከ9-12 transcript የentrance tempo እና የከፈልኩበትን አስገባሁ በpdf ኣርጌ ከዛ በአካል ስሄድ የ12ኡን copy ብቻ ነው የተቀበሉኝ አለቀ(የከፈልክበትን print ኣርገህ ይዘህ ሂድ)
Nov 16, 2023Call for Applicants to Undergraduate Extension Programs አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2016 ዓ.ም. በማታ መርሃ ግብር ለመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት 12ኛ ክፍል አጠናቃችሁ ለምታመለክቱ አመልካቾች አመልካቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይጠበቅባችኋል በ12ኛ ክፍል ውጤት የምታመለክቱ አመልካቾች ከ2011-2015 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መስፈርት መሰረት ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብን የምታሟሉ ከሆነ ከትምህርት ማስረጃ ጋር በማያያዝ ማቅረብ በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የሬሜዴያል ፕሮግራም ለወሰዳችሁ አመልካቾች 50%ና ከዚያ በላይ ዉጤት ያስመዘገባችሁበትን የሚገልጽ የትምህርት ማስረጃ ማቅረብ ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ከ2011-2015 ዓ.ም. ባለው ጊዜ በተለያየ ምክንያት አቋርጣችሁ ለምታመለክቱ የወጪ መጋራት ያጠናቀቃችሁበትን የሚገልፅ ደብዳቤ ከትምህርት ማስረጃ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብ አምጥታችሁ ወደተመደባችሁበት ዩኒቨርስቲ ያልሄዳችሁ ላለመሄዳችሁ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡ የማመልከቻ ሒደት የማመልከቻ ፎርሙን በዩኒቨርስቲዉ ድረገጽ (https:\\portal.aau.edu.et) መሙላት ከማመልከቻ ፎርም የሚያገኙትን የማመልከቻ ቁጥር (Application Number) በመያዝ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በቴሌ ብር ወይም በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ CBE ብር በ242424 አጭር ኮድ ክፍያ መፈጸም ክፍያዎትን ካጠናቀቁ በኋላ ወደማመልከቻ ፎርሙ በመመለስ በፒዲኤፍ (PDF) ፎርማት የተለወጠ የትምህርት ማስረጃዎትን የወጪ መጋራት ካጠናቀቁበትን ሰነድ ጋር መላክ፤ ማመልከቻዉን ካጠናቀቁ (Application complete) በኋላ የትምህርትማስረጃዎቹን ከማመልከቻ ቁጥርዎ (Application Number) ጋር በአካል ይዞ በመቅረብ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የሬጅስትራር ሕንፃ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 ማስገባት ይኖርብዎታል፡፡ ማሳሰቢያ የተማሪዎች ቁጥር ከመቀበል አቅም በታች (ዝቅተኛ) የሆነበት የትምህርት ፕሮግራም የማይከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ የአመልካቾች የመግቢያ ነጥብ በ2011 ዓ.ም. የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና ወስደው 295 እና ከዚያ በላይ ያላችሁ፡፡ በ2012 ዓ.ም. የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና ወስደው በተፈጥሮ ሳይንስ (English, Aptitude, Mathematics and Physics) 140 እና ከዚያ በላይ ያላችሁ፡፡ በ2012 ዓ.ም. የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና ወስደው ማህበራዊ ሳይንስ (English, Aptitude, Mathematics and Geography) 140 እና ከዚያ በላይ ያላችሁ፡፡ በ2013 ዓ.ም. የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና ወስደው 330/320 እና ከዚያ በላይ ያላችሁ፡፡ በ2014 ዓ.ም. የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና ወስደው በተፈጥሮ ሳይንስ 350 እና ከዚያ በላይ ያላችሁ፡፡ በ2014 ዓ.ም. የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና ወስደው በማህበራዊ ሳይንስ 300 እና ከዚያ በላይ ያላችሁ፡፡ በ2015 ዓ.ም. የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና ወስደው በተፈጥሮ ሳይንስ 350 እና ከዚያ በላይ ያላችሁ፡፡ በ2015 ዓ.ም. የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና ወስደው በአንደኛ ዙር በማህበራዊ ሳይንስ 300 እና ከዚያ በላይ ያላችሁ፡፡ የምዝገባ ቀን፡ ጥቅምት 27 እስከ ኅዳር 12 2016 ዓ.ም የምዝገባ ቦታ : በሬጅስትራር ህንፃ ቢሮ ቁጥር 203 አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2016 ዓ.ም. በማታ መርሃግብር ለመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት ሌላ ዲግሪ ኖሯችሁ ለምታመለክቱ በሙሉ አመልካቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይጠበቅባችኋል የወጪ መጋራት ካለ ያጠናቀቃችሁበትን የሚገልፅ ደብዳቤ ከትምህርት ማስረጃ ጋር ማቅረብ የማመልከቻ ፎርሙን በዩኒቨርስቲዉ ድረገጽ (https:\\portal.aau.edu.et) መሙላት ከማመልከቻ ፎርም የሚያገኙትን የማመልከቻ ቁጥር (Application Number) በመያዝ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በቴሌ ብር ወይም በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ CBE ብር በ242424 አጭር ኮድ ክፍያ መፈጸም ክፍያዎትን ካጠናቀቁ በኋላ ወደማመልከቻ ፎርሙ በመመለስ በፒዲኤፍ (PDF) ፎርማት የተለወጠ የትምህርት ማስረጃዎትን የወጪ መጋራት ካጠናቀቁበትን ሰነድ ጋር መላክ፤ ማመልከቻዉን ካጠናቀቁ (Application complete) በኋላ የትምህርትማስረጃዎቹን ከማመልከቻ ቁጥርዎ (Application Number) ጋር በአካል ይዞ በመቅረብ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የሬጅስትራር ሕንፃ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 ማስገባት ይኖርብዎታል፡፡ ማሳሰቢያ የተማሪዎች ቁጥር ከመቀበል አቅም በታች (ዝቅተኛ) የሆነበት የትምህርት ፕሮግራም የማይከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ በዲግሪያችሁ ለምታመለክቱ የመረጣችሁትን ትምህርት ክፍል የምታገኙት 12ኛ ክፍል ጨርሰው ያመለከቱ ከተመደቡ በኋላ በሚተርፉ ቦታዎች ላይ ብቻ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ በዲግሪያችሁ ለምታመለክቱ ኦፊሻል ትራንስክሪፕት ከተማራችሁበት ዩኒቨርስቲ በ1176 ፖ.ሳ.ቁ. በ EMS ወይም DHL ማስላክ ይኖርባችኃል:: የምዝገባ ቀን፡ ጥቅምት 27 እስከ ኅዳር 12 2016 ዓ.ም የምዝገባ ቦታ : በሬጅስትራር ህንፃ ቢሮ ቁጥር 203 አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራር
Nov 16, 2023