Hey all 👋 Entrance tefetnachu tiru yametachu please tebaberugn hasabachun 1. Endate batena effective mehon echlalew 2.Like bizu sew short note yilal Ena yemr asfelagi new Wey? 3.Ahun kemmarew kifl gar tnaten endate ekul lasked Please hasbachu betam yasfelgegnal zm endatlu 🙏 🙏 🙏
Nov 14, 2023Akay Girl ልምከርሽ ዝም ብለሽ አጥኚ በቃ እራስሽን ከአዳሪ እና ከግል ተማሪዎች Level አብቂ 1.አቅጂ ለምሳሌ ዛሬ ያለፈ ክላስ ምከልሺ ከሆነ እቅድ አውጪ ምሳሌ : 9 ነኛ ክፍል Math አንድ የሆነ Chapter.. Cover ለማድረግ አቅጂ በየሳምንቱ ወይም በየ5ቀኑ እቅድሽን መገምገም መከለስ 2.የራስሽ የሆነ የጥናት ስታይል ቢኖርህ ይህን ስልሽ ግን ከእንቅልፍ ከጤና ከውጤት አንፃር አይተሽ ቢሆን ጥሩ ነው የሌላም ሰው ስታይል ቢሆን ከጠቀመሽ ውሰጂው ለምሳሌ አንድ ጓደኛዬ ከክላስ እንደወጣ Nap ይወስዳል ከዛ እስከ ለሊት 8 ያጠናል ከዛ ተመልሶ ይተኛል ፣ ሌላኛው ጓደኛዬ ደግሞ ከክላስ እንደወጣ በዛው ያጠናል ግን እስከ 6 ነው የሚያመሸው አንዳንዶች ደግሞ ለሊት ይነሳሉ... በቃ ብቻ የጥናት የሕይወት ዘይቤ ልምድሽ አድርጊ 3. በቡድን የማጥናት ልምድ ይኑርሽ ይህ ለማስታወስ በጣም ይረዳሻል ሁለት ሶስት ጓደኞችሽ ጋር ሆነሽ በቃ ጥያቄ ፍለጡ ፣ አጥኑ ... 4.ስልክሽን ወይም ሶሻል ሚዲያን ለእውቀት ተጠቀመው Workbook ስራበት ፣ Ethio Matric ...Exam Veda ... ይህን ላንቺ አልነግርሽም ያው ስልክሽን ሌላ ወሬ ምናምን ላይ ሳታበዢ ለእውቀት ተጠቀሚው 5. አትሸበሪ፡ በትምህርት ሚኒስቴር የተለያዩ ዜናዎች ፣ በሀሰተኛ መረጃዎች ፣ በተደጋጋሚ ሞዴሎች አትሸበሪ አትደንግጭ ፈተና ሲደጋገም በጣም ይጠቅማል እና ደግሞ ሁሌም ዝግጁ ሁኚ ነገ ኢንትራንስ ነው ብትባይ እራሱ ለመፈተን የሚያበቃ Confidence እና አቅም ይኑርሽ ሞዴሎች ደግሞ ሲሰረቁ ቀድመሽ አትስሪ ራቂ አውቃለሁ ከተያዘ ውጤትሽን እንደሚያወርደው ግን አንቺ በደንብ ካጠናሽ ፈቀቅ አትይም ሌላው 6.ከማንኛውም መጥፎ ሱስ ራቂ አዎ ራቂ 7. Consistent ሁኚ ከላይ ያልኩሽን ነገሮች አታቋርጭ በቀጥታ ለረጅም ጊዜ የማድረግ ልምድ ይኑርሽ 8.short note ላልሽው ደግሞ አዎ በጣም ጠቃሚ ነው ካሁኑ መፅሐፍቶቹን ከቨር እያደረግሽ መሸምደድ ያለባቸውን ይረሳሉ የምትይውን አንድ Note book አዘጋጅተሽ ፃፊ በsubject ከፋፍለሽ ፈተና ሲደርስ ወይም ልትፈተኑ ስትሄዱ ይሄ በጣም እንደሚያስፈልግሽ ይገባሻል ከምር በደንብ ግን textኡን አንብቡ zn በመጨረሻም እግዚአብሔር ይርዳሽ ያው እኔ አዳሪ ነው የተማርኩት እና የጠቀሙኝ እና ደግሞ Consistency ቢኖረኝ ካሁኑ የተሻለ ውጤት ላመጣ የምችልበትን ነገሮች ነው የነገርኩሽ። እና ካንቺ ቢያንስ ከ 630 በላይ እጠብቃለሁ በርቺ🙌
Nov 15, 2023