Selam sewoch remedial universty keflo memar yechalal ende normal wetet yalmetalen pls negerugn metaku kalachu?😥
Nov 09, 2023✨ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ (ቀድሞ ለተመዘገቡ ተማሪዎች የመኝታ አገለግሎት እንሰጣለን!) አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የማጠቃለያ ፈተና ተፈትነው የማካካሻ ትምህርት/Remedial / ፕሮግራም ለመከታተል ያለፉትን ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት በግል ከፍሎ ለመማር የሚፈልጉ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡ 1. የመመዝገቢያ መስፈርቶች በ2015 ዓ.ም 12ኛ ክፍል አገር አቀፍ የማጠቃለያ ፈተና ተፈትነው የማካካሻ ትምህርት/Remedial/ ፕሮግራም ለመከታተል ያለፉ * ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች 210 እና ከዚያ በላይ * ለማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች 180 እና ከዚያ በላይ 2. የሚያስፈልጉ የትምህርት መረጃዎች 1.E.S.L.C.E EHEEQC የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመግቢያ ውጤት ካርድ ኦርጅናልና የማይመለስ አንድ ፎቶ ኮፒ 2. ከ9- 12ኛ ክፍል ትራንስኪሪፕት ኦርጅናልና የማይመለስ አንድ ፎቶ ኮፒ 3. የማይመለስ አንድ ዶስ (ክላሰር) እና ሁለት ጉርድ ፎቶ ግራፍ 4. የማመልከቻ ክፍያ ብር 50.00 /ሀምሳ ብር/ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካዉንት ቁጥር 1000021480502 ገቢ የተደረገበትን ደረሰኝ ከማስረጃቸዉ ጋር ማያያዝ:: 5. የስምንተኛ ክፍል ሚኒስትር ካርድ ኦርጅናልና የማይመለስ አንድ ፎቶ ኮፒ 3. የማመልከቻ ቦታ - አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ነጭ ሣር ካምፓስ የተከታታይና ርቀት ትም/ት ኮሌጅ ሬጅስትራር ጽ/ቤት 4. የምዝገባ ጊዜ - ከጥቅምት 26/2016 እስከ ህዳር 10/2016 ዓ.ም ድረስ ለተጨማሪ መረጃ - 046-181-5468 እና 046-181-0228 ማግኘት ይችላሉ:፡ 💥ቀድሞ ለተመዘገቡ ተማሪዎች የመኝታ አገለግሎት እንሰጣለን 💥የቀድሞ 12ኛ ክፍል ፈተናዎች እና ጥያቄዎች ይሠራሉ፡፡ 💥በተማሪዎች ጥያቄ መሠረት ያልገባቸውን ትምህርት እናስተምራለን፡፡ ምንጭ፡ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተከታታይና ርቀት ትምህርት ኮሌጅ
Nov 10, 2023