ከሷ ውጪ ሰው የማሰብ ሞራልም እቅድም አልነበረኝም። እያንዳኑ ሃሳቦቼ ላይ ተፅኖዋ ቀላል አልነበርም። ሰዎችን የምመዝነበት ሚዛን ሆና ነበር፥ ብዙ ሰዎች መጡ አስቀመጥኳቸው እሷን ግን ማንም ሊያንቀሳቅሳት አይችልም። እንዲ እንደዋዛ ቃላት አታባክንም ያወራችው ሁሉ ከነትዝታዋ አብሮኝ አለ ዝም ያለ ቃላት የማያባክን አንደበት አላት። መልኳን ለማሳመር ብዙ አትለፋም፥ ድብዝዝ ያለች ናት ሳያት ግን እፈዛለሁ። በዝታብኝ አታውቅም ሁሌም ላያት እጓጓለሁ። ለኛ እጋጣሚ ለፈጠሪ ግን እቅዱ የሚመስል የህይወት መንገድ ላይ ሲያገናኘን። ለእኔ ሚስት መሆን ያለባት እሷ ብቻ እንደሆነች አመንኩኝ። ስለፍቅር ተብሎ የትኛውንም መስዋዕትነት ብከፍልላ የሚገባት እንደሆነሆ ከልቤ ተማከርኩ። አንዱ ከወጣትነት ችኮላ ሰከን ብሎ ትክክለኛውን ጊዜ ጠብቆ የእጮኝነት ጥያቄ ማቅረብ ነበር። ጊዜ በሄደ ቁጥር ዋጋ ሊያስከፍለኝ እንደሚችል ገምቼ ነበር ግን አጉል አድርጌ ከማበላሸው ብታገስ ይሻላል በሚል የእጮኝነት ጥያቄዬን አዘገየሁት። አሁን ለዘላለም አጥቻታለሁ የሌላ ሆናለች። እንደምወዳት ራሱ አልነገርኳትም። ልክ እንደሰማሁ ጭንቅላቴን የተመታሁ ያህል ነው የተሰማኝ። ልክ ሰሃራ ወንም ናሚብያ በረሃ ውስጥ ራስን እንደማግኘት። ወደየት መሄድ እንዳለበት እንደጠፋው ሰው...
Nov 07, 2023Afen kefche new yanebebkut😭😭😭
Nov 07, 2023