ሰላም ዉድ ኢትዮጵያውያን ነገሩ እንደዚህ ነው በህይወቴ ሀዘን አጋጥሞኝ አያውቅም ሁሌም ደስተኛ ነኝ ለምን እንደሆነ ባላወቀም እና ጥያቄ የሆነብኝ አንዳንድ ቀናት በጣም ከመደሰቴ የተነሳ ራስህን አጥፋ አጥፋ ይለኛል። እናም ይሄ ነገር አጋጥሟችሁ የሚያዉቅ መፍትሔ ስጡኝ እስቲ " ብንሄድ ይሻለናል " ከማለቴ በፊት
Nov 06, 2023አጋጥሞኝ አያውቅም ግን ሊፈጠር እንደሚችል አቃለሁኝ አንዳንድ ሰዎች ይሄ ነገር በተዘዋዋሪ ያጋጥማቸዋል ማለትም እራሳቸውን ደስተኛ የሚያረጉበት ነገር ላይ ተመስርቶ ለምሳሌ ድራግ የሚጠቀሙ ሰዎች በሚጠቀሙ ወቅት እራሳቸውን ለማጥፋት ውስጣቸው ይገፋፋል አንዳንዶች ደሞ መጠጥ ጠጥተው ምናምን ለአይምሮ የሚከብድ ነገር ያረጋሉ ከፎቅ ላይ መዝለል ምናምን.......በሌላ በኩል ደሞ ቀጥታ ምንም ችግር የለብኝም ሁሌ ደስተኛ ነኝ ህይወት አንደኛውን ገፅታ ብቻ ታሳያቸዋለች ይሄንን ሽሽት እራሳቸውን ማጥፋት ሊፈልጉ ይችላሉ የኔ ምክር ይሄ ስሜት ሲሰማክ የተቸገሩትን ማሰብ እና የብዙ ሰው ችግር ያንተም እንደሆነ አስበክ ለሰው መኖርን ማሰብ አለብክ ይሄው ነው🙏
Nov 06, 2023