Hi everyone last year remedial yetmrachu i have a question.. first A.A medba ale wey le remedial temarwoch plus demo extension yekblalu a.a le remedial temrwoche
Nov 06, 2023በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2016 ዓ.ም. በማታ መርሃ ግብር ለመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት 12ኛ ክፍል አጠናቃችሁ ለምታመለክቱ አመልካቾች 📌አመልካቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይጠበቅባችኋል👇 💥በ12ኛ ክፍል ውጤት የምታመለክቱ አመልካቾች ከ2011-2015 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መስፈርት መሰረት ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብን የምታሟሉ ከሆነ ከትምህርት ማስረጃ ጋር በማያያዝ ማቅረብ 💥በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የሬሜዴያል ፕሮግራም ለወሰዳችሁ አመልካቾች 50%ና ከዚያ በላይ ዉጤት ያስመዘገባችሁበትን የሚገልጽ የትምህርት ማስረጃ ማቅረብ 💥ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ከ2011-2015 ዓ.ም. ባለው ጊዜ በተለያየ ምክንያት አቋርጣችሁ ለምታመለክቱ የወጪ መጋራት ያጠናቀቃችሁበትን የሚገልፅ ደብዳቤ ከትምህርት ማስረጃ ጋር በማያያዝ ማቅረብ 💥ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብ አምጥታችሁ ወደተመደባችሁበት ዩኒቨርስቲ ያልሄዳችሁ ላለመሄዳችሁ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡ 📌የአመልካቾች የመግቢያ ነጥብ👇 ⚡️በ2011 ዓ.ም. የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና ወስደው 295 እና ከዚያ በላይ ያላችሁ፡፡ ⚡️በ2012 ዓ.ም. የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና ወስደው በተፈጥሮ ሳይንስ (English, Aptitude, Mathematics and Physics) 140 እና ከዚያ በላይ ያላችሁ፡፡ ⚡️በ2012 ዓ.ም. የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና ወስደው ማህበራዊ ሳይንስ (English, Aptitude, Mathematics and Geography) 140 እና ከዚያ በላይ ያላችሁ፡፡ በ2013 ዓ.ም. የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና ወስደው 330/320 እና ከዚያ በላይ ያላችሁ፡፡ ⚡️በ2014 ዓ.ም. የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና ወስደው በተፈጥሮ ሳይንስ 350 እና ከዚያ በላይ ያላችሁ፡፡ ⚡️በ2014 ዓ.ም. የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና ወስደው በማህበራዊ ሳይንስ 300 እና ከዚያ በላይ ያላችሁ፡፡ ⚡️በ2015 ዓ.ም. የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና ወስደው በተፈጥሮ ሳይንስ 350 እና ከዚያ በላይ ያላችሁ፡፡ ⚡️በ2015 ዓ.ም. የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና ወስደው በአንደኛ ዙር በማህበራዊ ሳይንስ 300 እና ከዚያ በላይ ያላችሁ፡፡ ዝርዝር መረጃውን ያንብቡ👉 Click ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Nov 07, 2023