ሰላም! ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ ኢትዮጵያ ላይ ብዙ ክፉ ነገር ተሰርተዋል ይባላል፤ በማስረጃ የሚነግረኝ አለ?
Oct 04, 2020በአጠላቃይ ክፉ ናቸው ለማለት ይከብዳል፣ ግን ከሳቸው በፊት ከነበሩት አፄ ምኒልክ ጋር ሲወዳደሩ የገዙትን ዘመን ያህል እና የገዙበትን የስልጣኔ ደራጃ ስታይ ለሀገሪቱ ከሰሩት በላይ ለራሳቸው ስልጣን ማራዘም የሰሩት ይበልጣል። እምዬ ሚኒልክ እስከ 1903 ድረስ የሰሩት በጣም ብዙ ተራማጅ እና ኢትዮጵያን የቀየረ ነበር። አፄ ኃ/ስላሴ ግን ጣልያን መጥቶ ሀገሪቱን ለመጥፎ አላማው ሲል አለማው እንጂ እስከዛ ድረስ እሳቸው ልጅ እያሱንና ንግስት ዘውዲቱን ከዘውዱ በማራቅ ላይ ነበር ትኩረታቸው። ከጣልያን ወረራ በኃላ ግን በተሻለ ሁኔታ ለጥቂት ሰርተዋል። ይህ ሁሉ ግን እስኪሆን እድሜያቸው ጨምሮ ፣በኃይለኛ ፊውዳል አስተዳደር ተተብትቦ ህዝብን በከፍተኛ ሁኔታ ያስቀይም ጀመር። መሃይሙ የኢትዮጵያ ህዝብ ንጉስ የእውነት ስዮመ እግዚአብሄር ናቸው ብሎ ስለምያምን አንገቱን ደፍቶ ኖረ። 1953 የወንድማማቼቹ መፈንቅለ መንግስት ሙከራ በኃላ ንጉሱ ለካ ሰው ናቸው፣ ሰማይ አይታረስ ንጉስ አይከሰስ ለካ ማጃጃያ ነው ብሎ ተረዳ ህዝቡ። ከዛ በኃላ ወርቃማው የኢትዮጵያ ትውልድ የተወሰነ ያህል በዕውቀት በተመራ ሁኔታ ንጉሳዊ ስርዐቱን ሊገረስስ ቻለ። የሳቸው ዋና ስህተት የሚጀምረው ከስልጣን ወዳድነታቸው ነው። አፄ ምኒልክ አልጋ ያወረሰውን በአንፃሩ ተራማጅ የሆነውን ልጅ እያሱን፣ በእድሜ ካረጁ ራሶች ጋር በመተባበር ከስልጥን አውርዶ ንግስት ዘውዲቱን አንግሶ ራሱን የአዲስ አበባ ንጉስ ብሎ ሾመ። ግዜን ጠብቆ እሷን አውርዶ ራሱን ንግስና ቀባ። በጣልያን ወረራ ግዜ ባልተለመደ ሁኔታ ንጉስቱን ረስቶ ከአገር ሸሸ፣ በመሸሽ ላይ እያለ ጣልያን ልጅ እያሱን መልሶ ልያነግስ ይችላል ብሎ ገድሎት ሄደ። ከዛ በኃላ የወሎ ህዝብ በረሀብ ስያልቅ አይቶ እንዳላየ ሆነ። በ1962 የአአዮ የተማሪዏች ህብረት መሪን በግፍ አስገደለ…………
Oct 04, 2020