ሰላም። የእኔ እያቄ ለሙስሊሞች ነው። እኔ ምኖርበት ሰፈር ከቤተሰቦቼ ጋር ከገባን አስር ዓመት ይሆነናል እናም ድምፁ በቂ የሆነ አንድ መስጊድ ነበር። አሁን ግን ከየትና መቼ ይምጡ የማይታወቁ ብዙ ተከፍተዋል። ምን አገባህ ልትሉ ትችላላችሁ ነገር ግን በደንብ ነው የሚያገባኝ። ችግሩ ምን መሰላቹ አንዱ አዛን ብሎ ሲጨርስ አንዱ ይጀምራል። እንዲ እያለ እስካሁን የለየኋቸው 5 መስጊዶች ይጮሀሉ። በቃ ከማታ 12 ሰዓት ጀምሮ እስከ 2:30 መተኛት አይቻልም(አንዳንዴ ከዚያም ሊያልፍ ይችላል ምክንያቱ ሁሉም ነገር በእጃቸው ነው)። ሌሊት ደግሞ ከ11:00 በኅላ የተኛሁበትን ቀን አላስታውስም ድምፁ ከመጠን በላይ ስለሆነ ማለት ነው። ረመዳን ሚባለው ወር ሲመጣ ደግሞ ማታ እስከ 5:00 መተኛ የማይታሰብ ነው። ለደህንነቴ ሲባል ሰፈሬን መናገር አልችልም። ሰፈሩን ለቀን ብንን ብለን እንዳንጠፋ ደግሞ we can't afford. እና የኔ ጥያቄ ሀይማኖታቹ የሰላም ከሆነ ከስራ ደክሞት የሚመጣን ሰው እንቅልፍ መንሳት ትክክል ነው ብላቹ ታስባላቹ? የአዛን አላማ ሰፈርን ማናጋት ነው ወይስ ሰውን መጥራት? አንዱ ካሰማና በሌሎቹ ደግሞ ቢሰገድ ምን ችግር አለው? በቀናነት መልሱልኝ። I respect your religion.
Nov 02, 2023አዎ ሙስሊም ነኝ ተረዳሁህ ነብዩ ሰዐወ የጭ ሽንኩርት የበላ ራሱ መስጊድ እንዳይገባ ከልክለዋል በሽታው ሌላውን እንዳይረብሽ ማለት ነው ገባሃ ግን ሙስሊም ማለት ሁሉም መስሊም አንድ አደለም ብዙ አይነት አለው እና አይስማሙም መስጊዶቹም እያንዳይዳቸው ይለያሉ ለዛ ነው እልህ ተያይዘው እንጂ ተወያይተው በውይይት መፍታት ይችሉ ነበር በቃ ምን ልበልህ የሀበሻ ችግር ነው 🤷🥲
Nov 02, 2023