ከዚህ ቀደም የፊንጢጣ ኪንታሮት ወጥቶባችሁ የምታውቁ ወይም የሕክምና ባለሙያዎች ካላችሁ እንደዚህ አይነት ኪንታሮት ወጣብኝ እና በምን አይነት መልኩ ነው ሊድንልኝ የሚችለው? ስለ ኪንታሮት ምንም መረጃው የለኝም እና ስለ ሕክምናው እና ምን ያህል ብር እንደሚያስፈልገኝ እንዲሁም በምን ያህል ጊዜ ውስጥ ሕክምናዬን ማድረግ እንደሚገባኝ ብትነግሩኝ? ከሕክምናው ጋር ተያይዞ ሊመጣ የሚችል የጎን እዮሽ ጉዳት(Side effect) ካለ እርሱንም ላደርጋቸው ከሚገቡ ጥንቃቄዎች ጋር አያይዛችሁ ብትነገሩኝ? Thanks in Advance
Nov 02, 2023Bruh እኔም ከ6 ዓመቴ ጀምሮ እስከ 12 ዓመቴ ነበረብኝ በጣም ነው ሚያስቃየው ፊንጢጣህ አካባቢ መድማት መክሳት ብቻ ብዙ ብዙ ስቃዮች አሉት እና መድኃኒት እና ብዙ የባህል ህክምናዎችን ተጠቅሜ ነበር ግን ወፍ የለም finally ግን በ12 ዓመቴ mother ፀበል ይዛኝ ሄደች ከ 3 ሳምንት በላይ ተጠመኩ! ቀልድ ሊመስልህ ይችላል ግን መጠመቅ በጀመርኩ በ 3 ሳምንት አካባቢ ሽንት ቤት ሆኜ ከውስጥ ትልቅ ነገር ውልቅቅቅ ብሎ ሲወጣ ተሰማኝ finally ወጣልኝ ዳንኩ! እነሆ ከተሻለኝ 8 ዓመት አለፈኝ እግዚአብሔር ይመስገን🙏 እንደምንም ብለህ ፀበል ሂድ ሌላውን ነገር ተወው በደንብ እመንና ተጠመቀ ከዛ ሰላም ትሆናለህ bruh 🙌 በተረፈ እግዚአብሔር ይማርህ
Nov 02, 2023