Selam selam family👨👩👧 shortly, my story is fkregna alechign and she's a little bit of feminist ena mndnew yagatemagn🤭 betam inen mewededwan inde shenfet nw metekotrew and this is giving a space between us. So, what shall i do to keep this relationship? I need an advice
Oct 25, 2023በአጭሩ ስለ ፌሚንዝም 👩🦳👨👧👦👨👩👦 ፌሚኒዝም ማለት ትርጉም አልባ ና በምዕራቡ አለም ቤተሰብን ጨርሶ ያጠፋ ነገር ነው:: 7 ትላልቅ ጉዳቶቹ ፦ 1. ከኔ በፊት ቅድሚያ ለቤተሰቤ ከምትል ይልቅ በጣም ራስ ወዳድ የሆነች እናት (ፍቅረኛ) የሚፈጥር 2. አባትን፣ ወንድምን እና ወንድ ጓደኛን በአጠቃላይ ወንድ የተባለን ፍጥረት እንደ አስገድዶ ደፋሪ መመልከት 3. ሴቶች ትዳርን እንዲጠሉ እና ከትዳራቸው በአልባሌ ምክንያት እንዲፋቱ በማበረታታት በኋላም ከባድና የቁጭት ህይወት እንዲኖሩ መዳረግ 4. ሴቶች "ልጅ የሚያስወልደኝ እንጂ አባት አያስፈልግም" የሚል አፀያፊ አቋም እንዲይዙ ጥላቻን በማስተማር ያለ በቂ ምክንያት "ሲንግል ማም" እንዲሆኑ መዳረግ። ዋና አላማው ልጆች የአባታቸውና የእናታቸውን ፍቅር ሳያገኙ እንዲያድጉ ማድረግ ነው 5. ወንዶች በሴቶች ላይ የሚደርሱ ወንጀሎችን ለመከላከል(ለፍርድ ለማቅረብ) ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳላቸው እየተወቀ ጭራሽ እነሱን በጅምላ በመስደብና በመፈረጅ "ምን አገባኝ" ወደሚል መጥፎ ሀሳብ እንዲገቡ ማድረግ 6. በሴቶች እህቶቻችን ላይ የሚደርሰን "ማንኛውም" አይነት ወንጀል ሴት ስለሆነች ብቻ ነው የደረሰባት በሚል ጭፍን አመለካከትና በሚገርም ሁኔታ ጥፋቱን የፈጽመውን ግለሰብ ለህግ እንዲቀርብ ከመስራት ይልቅ ሁሉንም ወንዶች በጭፍን በመወንጀል የባሰ ጥላቻን መፍጠርና በተዘዋዋሪ ወንጀሉ እንዲበራከት መስራት 7. በሴቶችና ወንዶች መካከል ጥላቻ እና ቅራኔን በማብዛት ቤተሰብ እንዳይቀጥል የሚያደርጉ እጅግ "ልቅ" ተግባራት እንዲበራከቱ ማድረግ በአጠቃላይ ይህ አሰተሳሳብ እጅግ ሰይጣናዊ፣ መርዛማ እና ከቤተሰብ እስከ አገር የሚያፈርስ ነው። ፌሚኒስት ነን የምንል ፈጣሪ ልቦና ይስጠን 🙏 በተለይ ባለማወቅ ፋሽን አድርገነው የነበርን::
Oct 25, 2023