እባካችሁ እርዱኝ መኖር በጣም እያስጠላኝ ነው.....porn አያለሁ masturbateም አደርጋለሁ መኖር በጣም እየፈራሁ ነው ምንም እራሴ ላይ መስራት አልቻልኩም አንድ ነገር ሰምቼ action ላይ ዜሮ ነኝ......የወደፊት ህይወት ምንም አይታየኝም ተስፋ ቆርጫለሁ....ዘንድሮ ደግሞ 12th ነኝ ማጥናት በጣም ነው ሚያስጠላኝ.....ለወደፊቴ ተስፋ ቆርጫለሁ እባካችሁ እርዱኝ.....
Oct 24, 2023ኧረ ወገን እያሰብን 🙆♀! 12ኛ ክፍል ማለት እኮ የህይወት ምዕራፍህን ሙሉ በሙሉ ባይሆንም አብዛኛውን መጪ ህይወትህን ምታስተካክልበት ነው ይሄ ጊዜ አልፎ እንዳይቆጭህ እኔ ካሳለፍኩት ነገር ነው ምመክርህ ጎበዝ ለብዙ ነገር ምትጠበቅ የደረጃ ተማሪ ነበርኩ ግን 12ስደርስ የሚያሳስበኝ ቀጣዩ ህይወቴ ሳይሆን day ማክበሩ , ራስን መጠበቁ እና senior መምሰሉ ላይ ሆነ እና ጫፍ ላይ እንደነበርኩ ሳይታወቀኝ ፈተናውን ተፈተንኩ እና በሚያሳዝን ሁኔታ አላለፍኩም ለሱ ዋጋ እከፍልበታለሁ 1 አመት መስዋዕት አርጌ እማራለሁ ምንም ቢመጣ ተስፋ አልቆርጥም መዘናጋት ባይኖር ግን ይሄ ሁሉ ባልሆነ ነበር እና ....የማይደርስ ምትመስለን ያቺ ቀን ትደርሳለች(ግንቦት ማለት አሁን ቅርብ ነው) አሁንም ከተኛህበት ለመንቃት አልረፈደም ስልክህ ላይ ያሉትን እንደዚህ አይነት ነገሮች ጨክነህ አጥፋ (porn video , GIF ...) searchም አታርግ ይሄ ስለ12ኛ ክፍል ብቻ አይደለም ስለ ሙሉ እድሜ ዘመንህ ዋጋ ትከፍልበታለህ ! በጠዋት መነሳት ልመድ ስፖርት ስራ(ንቁና ደስተኛ ያረጋል), social relation አስፋ , ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ምትከታላቸው motivation የሚናገሩ ሰዎች ቢሆኑ (ስኬታማ ሰዎች) , ቴሌግራም እና ቲክቶክ(ስራ አስፈቺ ነገሮችን ) ብትቀንስ ምናምን አሪፍ ነው ባይ ነኝ ትክክለኛ senior ድርሻው ይሄ ነው ወንድሜ ከኔ ተማር በሇላ ላለመፀፀት . (ሴትም ከሆንሽ እንደዛው ) plzz ራሳችንን እናድን😭😭😭!
Oct 25, 2023